ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ከእሳትና ጥይት የተረፉት ታሳሪዎች በቂሊንጦ በእንግልትና ስቃይ ውስጥ ናቸው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ከእሳትና ጥይት የተረፉት ታሳሪዎች በቂሊንጦ በእንግልትና ስቃይ ውስጥ መሆናቸውን ለቢቢኤን ገለጹ

ቂሊንጦ በደረሰው የእሳትና የጥይት ተኩስ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ መንግስት ባመነው 23 ሰዎች እና ከዚያ በላይ መሞታቸው ይታወቃል፡፡ የተረፉት እስረኞች ወደ ተለያዩ እስር ቤቶች መላካቸው እና የተወሰኑት ደግሞ በቂሊንጦ ታስረው እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በቂሊንጦ የተመደቡት እስረኞች በአንድ ክፍል ተዘግቶ እንደሚውሉ ና በቂ የጸሃይ ብርሃን እንኳን እያገኙ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ ለቤተሰብ ጥየቃ ከተፈቀደችው ትንሽ ደቂቃ ውጭ በአንድ ክፍል ተዘግቶባቸው እንደሚውሉና በማእከላዊ እንኳን ለጻሃይ ብርሃን በቀን የሚሰጠው ደቂቃዎች ለነሱ መነፈጉን የታሳሪ ቤተሰቦች አስረድተዋል፡፡

የቆዪ ብርድልብሶች እንዲሁም ክፍሎች ተዘግተው ስለሚውሉ አንዳንዶች የጤና መታወክ ጭምር እያጋጣማቸው መሆኑን እና ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ጠቁመዋል፡፡ ማህበረሰቡም የታሳሪዎች የየአያያዝ ሁኔታ እንዲስተካከል ግፊት እንዲያሳድር ሲሉ መልክታቸውን ልከዋል – ቢቢኤን መስከረም 7/2009