በወልቃይት ዐማሮች ላይ በአዲስ ዓመት ምሽት ተኩስ ሲዘንብባቸው አምሽቷል
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በወልቃይት ዐማሮች ላይ በአዲስ ዓመት ምሽት ተኩስ ሲዘንብባቸው አምሽቷል
ዛሬ መስከረም 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ምሽት በወልቃይት አዲ ረመጥ ከተማ አዲስ ዓመቱን የተወሰዉ ወገኖቻቸውን በማሰብ በቤታቸው ሲያከብሩ ውለዋል፡፡ ምሽት 3፡00 ሲሆን የትግራይ ልዩ ኃይል ፖሊስ የዐማራ ተወላጅ በሆኑ ቤተሰቦች ቤት ላይ ጥይት መተኮስ ጀመረ፡፡ የወልቃይት ወጣቶች ምንድን ነው በማለት ከቤታቸው ወጡ፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት እኩለ ሌሊት ድረስ በዐማሮች ላይ ተኩስ የተከፈተ ሲሆን ወጣቶች የአጸፋ መልስ አልሰጡም፡፡
ከአዲ ረመጥ ከተማ እኩለ ሌሊት ላይ መረጃውን የሰጡን ሰዎች በምን ምክንያት ይህ ተኩስ ሊፈጠር እንደቻለ ላነሳንላቸው ጥያቄ ‹‹ዛሬ የአዲስ ዓመት በመሆኑ ብዙ የወልቃይት ልጆች ይመጣሉ በሚል አስቀድሞ ዝግጅት ነበር፤ ወደ ምሽት አካባቢ መረጃው ደርሶናል፡፡ ምንም ዝግጅት ባላደረግንበት ወጣቶች የአጸፋ መልስ ሰጥተው ቢሆን ኖሮ በመከላከያ ሰራዊትና በፖሊስ በተቀነባበረ ኦፕሬሽን ዐማሮችን በጅምላ ለመጨረስ የታቀደ ነው፡፡ ሆኖም አላስፈላጊ መስእዋትነት ላለመክፈል ወጣቶቻችን እንዲሸሹ አድርገናል፡፡ አሁን የሞተ ሰው ስለመኖር አለመኖሩ የምነግርህ ነገር የለም›› ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ አቶ ዘነበ ፋንታና አቶ ተስፋየ የተባሉ ዐማሮች እከለ ሌሊት ታፍነው ተወስደዋል፡፡
አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም ‹‹አዲስ ዓመት በሰላም የሚያከብረው ትግሬ ብቻ ሆኖ እስከመቼ እንደሚቀጥል የምናየው ይሆናል›› ሲሉ ቁጭታቸውን ገልጸዋል፡፡