ዳን አድማሱ በ EBC በቀጥታ በተላለፈው የአዲስ አመት ዋዜማ ዝግጂት ላይ የኢትዮጵያ ህዝብን ተቃውሞ አስተጋባ!!!
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።

ዳን አድማሱ በ EBC በቀጥታ በተላለፈው የአዲስ አመት ዋዜማ ዝግጂት ላይ በመገኘት የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ምልክትን በማሳየት እና ወኔ ቀስቃሽ ዘፈኖቹን ብቻ በመዝፈን በራሱ በወያሌ ሚዲያ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብን ተቃውሞ አስተጋባ!!!
ብዛት ያላቸው አርቲስቶች ሰው እየተገደለ እኛ አንዘፍንም በማለት የህዝብ ልጅነታቸውን አስመስክረዋል! በዚህም አክብሮታችን የላቀ ነው!! ዳን አድማሱ ደግሞ በተለየ መንገድ ወያኔ ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጦ ተቃውሞውን አሰምቷል፣ አሳይቷል!! ሙዚቀኞቹም እንደዚሁ ጥቁት በመልበስ አብረውት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል!
ዳን በመድረክ ላይ ከዘፈናቸው ዘፈኖች መሀል የተወሰደ ግጥም፡-

የከፋሽ ይመስላል ምነው… ምነው
አዝኗል ለካስ ልብሽ ደስታም የለው
ላዘን ፊት አትስጭው ጭራሽ
ሂዎት ላትኖሪያት ደግመሽ
ለኔ ደስታየ ነው ብታይ
ምንም አይኔ ከፍቶሽ ባላይ
…
ለቀን አለቃ ቀን አለውና
አሮጌው ባዲስ ይተካል ገና
!
እናመሰግናለን የህዝብ ወገንተኝነትህን በተግባር ዋጋ ከፍለህ ያሳየኸን ዳን አድማሱ!!!
ይህን እና መሰል ወኔን ቀስቃሽ መረጃ በማስተጋባት የተሰበረው የፍርሀት ሰንሰለት ዳግም እንዳይጠልቅብን አርቀን እንድንጥለው ይሁን!!!

#Minilik Salsawi