ዘበነ ለማ ቤተክርስቲያን እንዲረክስ አደረገ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ከታዛቢ፤ ዋሽንግተን ዲሲ
- በዛሬው ዕለት በስደተኛ በሚተዳዳረው አንጋፋው የሜሪላንድ ደብረ ገነት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ውስጥ የወያኔው ተላላኪ አባ መላኩ (ፋኑኤል) እንዲመጡ በማድረግ ቤተክርስቲያኑን እንዲረክስ አድርጓል
- አንጋፋው የሜሪላንድ ደብረ ገነት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ምዕመና ለምን ቤተክርስቲያናቸውን መቆጣጠር ቸል እንዳሉ ብዙዎችን እያጠያየቀ ይገኛል
ጳጳሳት፣ካህናት፣ መምህራንና ዲያቆናት የሕዝብን ብሶትና እሮሮ የሚያዳምጡ፣ የህዝብን እንባ የሚያብሱ፣ በህዝብ ላይ የሚደርሰው ግፍና መከራ የሚያንገበግባቸው፣ ህዝቡ ሲመታ የሚያማቸው፣ ሕዝቡ ሲደማ አብረው የሚደሙ፣ ህዝቡ ሲያለቅስ አብረው የሚያለቅሱና በአጠቃላይም የህዝብ አካልና አምሳል መሆን እንደሚገባቸው የማይታበል ሃቅ ነው። የሃይማኖት አባቶች ክፉ ስራ የሚሰሩ ገዥዎችንም ሆነ ማንኛውንም ግፈኛ መገሰጽና ማውገዝ ይገባቸዋል። ያነገቡት ወንጌልና ደረታቸው ላይ ያንዠረገጉት መስቀል የሚያዛቸውም ለእውነት እነዲቆሙና እውነትን እንዲመሰክሩ ነው። ወንጌሉም የሚያዛቸው ለፍትህና ርትህ እንዲቆሙና ለተበደለውና መከራ ለሚወርደበት ክፍል ተቆርቋሪና አለኝታ እንዲሆኑ ነው።ይህንን ከላይ የተዘረዘሩትን መልካም ሥራዎች በብቃት የሚያከናውኑ የሃይማኖት አባቶች እንደ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ፣ እንዲሁም አሁን በቀርቡ ሥራቸውን እያየን የመጣነውን እንደ መምህር አሸናፊ ዱጋ ያሉና ሌልችም እንዳሉ አይካድም።
በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚገኙ ካህናትና መምህራን የሚሰሩት ሥራ ግን ከዚህ ተቃራኒውን ሆኖ መመልከት እጅግ ያበግናል። ኢትዮጵያ አገራችንን በአሁን ሰዓት በውጭ ወራሪ እንደተያዘች ያህል ንጹሃን ወገኖቻችን በጥይት እየተቆሉ፣ እጅግ ጭካኔ በተሞላው ሁኔታ ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው ይገኛል። አለወንጀላቸው የታሰሩ ንጽሃን በር ተቆልፎባቸው በእሳት እየጋዩና ቦንብ እየፈነዳባቸው፣እናት የልጇ አስከረኔን ላይ ተገፍትራ ወድቃ በቆመጥ እየተቀጠቀጠች ተሰባብራ ተጥላ እንዲሁ አባት፣እናት፣ዘመድ አዝማድ የሟች ዘመዶቻቸውን አስከሬን አፈር እንዳያለብሱ በታጣቂዎች ሰደፍ እየተፈነከቱ ባለበት ጊዜና በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ የመከራውን ጽዋ እየጨለጠ ባለበት ወቅት አይናቸው እየተመለከተና ጆሯቸው እያዳመጠ ምንም ሳይመስላቸው ከገዥዎች ጋር ተቃቅፈው ሕዝብ የሚያስጨርሱ የኃይማኖች አባት ተብዬዎችዎን መቼ ነው ህዝብ በቃችሁ የሚላቸው?
በውጭው ዓለም ያለው ሕዝብ በአገሩ ጉዳይ ላይ ጠንካራ አቋም እንዳይወስድና ወያኔ ላይ ቁርጠኛ አቋም እንዳይኖረው እንዲሁም ለአገሩ ገንቢ አስተዋጾ እንዳያበረክት እንደ ዘበነ ለማ ያሉት ካድሬዎች “ፖለቲካ ውስጥ አንገባም” በሚል ማዘናጊያ ህዝቡን እግረ ከወርች ጠፍረው አስረውታል። ዘበነ ለማ ሰሞኑን እንኳ በተለያየ የአገሪቷ ክፍሎች የሚወርደው የደም ጎርፍ ምንም ሳይመስለው የኢትዮጵያ ህዝብ ማቅ ለብሶ ሀዘን ላይ በተቀመጠበት ወቅት በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ምዕመናንና ካህናት ነጭ ለብሰው አሸብርቀው ለአዲስ ዓመት በዓል ዝግጅት ላይ እንዲምነሸነሹ እየቀሰቀሰ ይገኛል። ሙዚቀኞች መተዳደሪያ ገቢያቸውን በመተው የአዲስ ዓመት መቀበያ ዝግጅታቸውን እየሰረዙ በወያኔ ጥይት ለረገፈው ወገናቸው የሃዘን ተካፋይነታቸውን እየገለጹ ባለበት ወቅት የነዘበነ የድግስ ጋጋታ ምን ይባላል? ከታሪክ አለመማር ነው እንጅ ይህ የመከራ ጊዜ ሲያልፍ ዘበነ ለማና አቸፍቻፊዎቹ እንዲሁም ይህ እንዲፈጸም ያደረጉ የቤተክርስቲያኑ የቦርድ አባላት ምን ይሉ ይሆን? ያኔ በሰሩት ስራ ማፈራቸውና መጸጸታቸው አይቀርም።
እነ ዘበነ የንቀታቸውና የጥጋባቸው መጠን ፈር መልቀቁን የሚያሳየው ካድሬውንና የወያኔ ተላላኪውን “አባ መላኩን” ቤተክርስቲያን ድረስ በማምጣት “ዓለምን ለተውት፣ አገርን ለሚጠብቁ፣ ቤተክርስቲያናችን ለሚጠብቁ አባቶቻችን (ለነአባ መላኩ) እድሜ እንጸልይ፣ የሙሴ በትር የያዙ” እያለ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለውን ንቀትና ለወያኔ ያለውን ታማኝነት በግላጭ እያሳየ ይገኛል። ጉድ ሳይሳማ መስከረም አይጠባም ማለት ይህ ነው። አባ መላኩ ህዝብን በመበጥበጣቸውና በገንዘብ ስርቆሽ ምክንያት የሃዋሳ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ያባረራቸው መሆኑ አይዘነጋም። አባ መላኩ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ በቅርቡም ናሽቪል፣ ቲኔሲ ውስጥ ብጥብጥና ክፍፍል በማስነሳት ፍርድ ቤት ተከሰው እየተመላላሱ ሲሆን ምዕመናን የወያኔ ተገዥ ለማድረግ እንቅልፍ አጥተው መርዛቸው እየረጩ ይገኛሉ። በአባ መላኩ የሚመራ ህዝብ ሙሴ መርቶ የቃልኪዳኑን ምድር እንዳሳያቸው እንደ እስራኤላዊያን ሳይሆን ወደባቢሎን ምድር ገብተው እንደጠፉት እንደ ሰዶምና ገሞራ ነው የሚሆነው። አባ መላኩ እንደ ጣራ መቀደድና በአውደ ምህረት ላይ መቀላመድ ልማዳቸው የሆነን ሰው ቤተክርስቲያን አምጥቶ ማስረከስ ምን ይባላል? ዘበነ ለማ ከዚህ ጋር የተያያዘው ቪዲዮ ላይ እንደተመለከተው አባ መላኩን ሲያሞካሽና ሲያሸረግድ ያዳምጡ።