የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ሰብሳቢ አቡብክር አህመድን ጨምሮ ዘጠኝ በሱ መዝገብ የተከሰሱ ጀግኖቻችን ሁለት ሴት ታሳሪዎች ተፈቱ ከቤተሰብ ጋር ተቀላቀሉ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ሰብሳቢ አቡብክር አህመድን ጨምሮ ዘጠኝ በሱ መዝገብ የተከሰሱ ጀግኖቻችን ሁለት ሴት ታሳሪዎች ተፈቱ ከቤተሰብ ጋር ተቀላቀሉ
አህመዲን ጀበል፤አህመድ ሙስጠፋ፤ካሊድ ኢብራሂም፤ሙሃመድ አባተ ሌሎች በሌላ መዝገብ የተከሰሱ በርካታ አልተፈቱም
መንግስት ለፕሮፖጋንዳ ለመስራት እንዲመቸው ተፈቺዎችን ለሁለት ቀናት ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ታውቋል

Minilik Salsawi's photo.

ቢቢኤን ጷግሜ 4 /2008
መንግስት በመላው ሀገሪቱ ከሙስሊሙ በተጨማሪ በሌሎችም በተቀሰቀሰበት ተቃውሞ ውጥረት ውስጥ በመግባቱ ለማርገብ ከአዲሱ አመት ጋር በማያያዝ ኡስታዝ አቡበክርን ጨምሮ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፤ኡስታዝ በድሩ ሁሴን፤ሸህ መከተ ሙኄ፤ኡስታዝ ሰኢድ አሊ፤ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው፤ሙባረክ አደም፤ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ፤ኡስታዝ ሙራድ ሹኩር እንዲሁም ጀግናዋ መሬም ሃያቱ፤ ሃያተል ኩብራ ፤ ቶፊቅ ሙሃመድ፤ሙባረክ ከድር፤አብዱልመጂድ እና ሌሎችም በኤልያስ ከድር መዝገብ የተከሰሱት ከተፈቺዎቹ መካከል ናቸው፡፡ ለቤተሰቦቻቸው እና ለሙስሊሙ ማህበረሰብ እንኳን ደስ አለን እንላለን …አልሃምዱሊላህረቢል አለሚን


በተያያዘ ዜና መንግስት ፕሮፖጋንዳ ለመስራት እነሱን ከህዝበ ሙስሊሙ ለመነጠል እንዲያመቸው ከመፈታታቸው በፊት ሀሙስ እና ጁምአ በአዳራሽ ውስጥ ተፈቺዎችን በመሰብሰብ ስልጠና መስጠቱ ታውቋል፡፡ በዚሁ ስብሰባ ላይ ጀግኖቻችንም አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን መንግስት ለፕሮፖጋንዳ እንዲያመቸው የተናገሩትን ቆራርጦ ይቅርታ ጠየቁ ፤ከመንግስት ጎን እንደሚቆሙ ገለጹ በቴሌቪዥን ቢያሳይ ህዝብ ይህንን የተለመደ የመንግስት የውሸት ፕሮፖጋንዳ እንዲረዳ ሲል ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ ከመፈታታቸው በፊት ጀምሮ የመንግስት ካድሬዎች ጥሩ ውይይት ተደረገ ፤ይቅርታ ጠየቁ እያሉ ህዝብን ለማደናገር የሞከሩትም ህወሃታዊ ሴራ መሆኑ እንዲረዳ ስንል ለማሳወቅ እንወዳለን