ሕወሓት የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮ/ል አስራት በለጠን ከስልጣኑ አነሳ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ሕወሓት የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮ/ል አስራት በለጠን ከስልጣኑ አነሳ።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮ/ል አስራት በለጠን ከስልጣኑ ማንሳቱ ታውቋል። ኮ/ል አስራት በለጠ ከስልጣኑ የተነሳው ባለፈው የደብረ ማርቆስ ሰልፍ በተካሄደበት ወቅት «አጋዚ አትላኩ የኛዎች ይበቃሉ፤ አጋዚ ከገደለ ጦርነቱ የሚሆነው ከእኛ ፖሊሶች ጋር ነው» ብሎ በመናገሩ ነው። እስካሁን ድረስ ግን በኮ/ል አስራት በለጠ ቦታ የተተካ ሰው የለም። የኮ/ል አስራት በለጠ መነሳትም ይፋ አልሆነም።

የኮ/ል አስራት በለጠን ከስልጣን መነሳት የሰሙ የደብረ ማርቆስ ከተማ ነጋዴዎች  ኮ/ል አስራት በለጠ ለህዝብ በመወገኑ ተደስተው ወያኔ ለኮሎኔሉ ይከፍለው ከነበረው ደሞዝ በሶስት እጥፍ በመጨመር የነጋዴዎች ምክር ቤት ውስጥ በሀላፊነት ሊቀጥሩት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።