በወገራ የሕወሓት ወታደሮች ሕጻናትን ሁሉ እየጨፈጨፉ ነው – ሽንዲ ወያኔዎች ከዐማራው ላይ ይፋ ጦርነት እያካሄዱ ነው፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በወገራ የሕወሓት ወታደሮች ሕጻናትን ሁሉ እየጨፈጨፉ ነው፤በሰሜን ጎንደር የሕወሓት ወታደሮች ሁሉንም ዐማራ በእድሜ ሳይለዩ እየጨፈጨፉ ሲሆን ሕጻናት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ እስካሁን ድረስ ባለን መረጃ የ፮ ሕጻናት አስከሬን ጎንደር ዩንቨርሲቲ ሆስፒታል እንደገባ እና ከ፳ በላይ የሚሆኑ ምንም የማያውቁ ልጆች ሆስፒታል እንደገቡ የተጎጅ ቤተሰቦች አረጋግጠዋል፡፡

በወንበርማ (ሽንዲ) ወረዳ ወያኔዎች ከዐማራው ላይ ይፋ ጦርነት እያካሄዱ ነው፡፡ እስካሁን ሦስት ወንድሞቻችን ተሰውተዋል፡፡ የወንበርማ (ሽንዲ) ሕዝብ ለሁለት ተከታታይ ቀናት አደባባይ በመውጣት ከአገዛዙ ጋር እየተጋደለ ነው፡፡ መንገዶች ዝግ ናቸው፡፡በምእራብ ጎጃም ቡሬ ባለቤትነቱ የሕወሓቱ ቀንደኛ አባልና ሰላይ የሆነ ትንሳኤ የሚባለው ሆቴል ግቢ ውስጥ ሁለት ዐማሮች ተገድለውና ሸንኮራ አገዳ ቅጠል በላያቸው ላይ ተደርጎ ተገኘ፡፡ የሕወሓት ሰዎች ንብረት በሆኑ በዐማራው አካባቢ ተመሳሳይ ግድያዎች እንደሚኖሩ ይጠበቃል፡፡ Minilik Salsawi – mereja.com