በብዙ የዐማራ አካባቢዎች የመንግሥትን መዋቅር ሕዝቡ ተረክቧል፤ የጎበዝ አለቃዎች ጸጥታ የማስከበሩንና የመሪነት ሚናውን በሚገባ እየተወጡ ነው
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በዚህ ሁሉ መካከል ግን ሊወሰዱ የሚገባቸው ነገሮች አሉ፡፡ የዐማራው ሕዝብ መንግሥት መፍረሱን ተቀብሎ የሰላም ማስጠበቁን የመረከብ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ አዳዲስ የወረዳ አስተዳዳሪዎችና የጦር አበጋዞች መመረጥ አለባቸው፡፡ ሕዝቡ ደግሞ በመረጣቸው የጎበዝ አለቆች የመመራት ባሕሉን አጠናክሮ መሄድ አለበት፡፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ ምርጥ መሪዎች ሕዝቡን ወደ ፊት ይዘው መሔዳቸውን እናያለን፤ የቋሪትና የበለሳ ተመክሮ እንደሚስፋፋ እሙን ነው፡፡
የዐማራው ገበሬ ለማይወክሉት የወያኔ ተላላኪዎች የመሬት ግብርና የማዳበሪያ፣ የአብቁተ ብድር ምናምን መክፈል የለበትም፡፡ ሁላችንም የዐማራ ልጆች ለገበሬ ዘመዶቻችን የማስረዳት ኃላፊነት አለብን፡፡ ሁሉም ገበሬ በየበቀበሌውና በየወረዳው አስተዳደር የሥልጣን እርከኖችን በልጆቹ የማስያዝ ሥራ አሁኑ መጀመር አለበት፡፡
በቀጣይ ቀናት ማናቸውም የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት በመላው የዐማራ አካባቢ እንደሚቋረጥ ይጠበቃል፡፡ የስልክና የኢንተርኔት መቋረጥ በውጭ ያለውን የአክቲቪዝም ሥራ የሚጎዳው ቢሆንም በአገር ውስጥ ያለውን ትግል ግን ወደ ኋላ አይመልሰውም፡፡ የዐማራ ሕዝብ የወያኔን ቂመኛነት ከማንም በላይ ያውቀዋል፤ በዚህም ወያኔ ይቅር ለእግዜር የሚባልበት የይቅርታ ዘመን አልፏል፡፡ የመጨረሻው መጀመሪያ እንዲህ ነው!!
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!!