“የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርታና ክብር ኣይገባውም ። በፍጹም ይቅርታ አልጠይቅም! ” የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ጊዜው የደፋር፣ የይሉኝታ ቢስ እና የውሸታም ነው።

አትሌት አልማዝ አያና ዶ/ር ኢ/ር መሰለ ሀይሌ
ሰውየውን ጠዋት በሰይፉ ፋንታሁን ፕሮግራም ሰማሁት። የመጨረሻ ጥጋበኛና ውሸታም ነው። መልሱ ሁሉ የትዕቢት ነው። የድፈረቱ ድፍረት “ውጤቱ ጥሩ ነው እናንተ ጋዜጠኞች ይቅርታ ጠይቁ” ይላል። የማነው ዓይን አውጣ። ግን ምን ያድርግ ጊዜው የደፋር፣ የይሉኝታ ቢስ እና የውሸታም ነው። በነገራችን ላይ የሱ የኢንጂነሪግ ዲግሪ አይደለም። ጥያቄው በሪዮ ኦሊምፒክ በአትሌቲክ ስለመጣው ደካማው ውጤት እንደ ተቋሙ ፕሬዘዳንነት ሃላፊነት ይወስዳል ብለን ጠብቀን ነው።
“ሁለት ወርቅ ባለማሸነፌ ህዝቡን ይቅርታ እጠይቃለሁ” –አልማዝ አያና
“በፍጹም ይቅርታ አልጠይቅም! ብትፈልጉ እናንተ ይቅርታ መጠየቅ ትችላላቹ..አትሌቲክሱ ወድቋል የምትሉ! ጥሩ ውጤት ነው ያመጣነው”- ዶ/ር ኢንጂነር መሰለ ሀይሌ (የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት)
…
ትንሽ ክብር…ትንሽ አንገት መስበር…ትንሽ ትህትና…ይበቃን ነበር ቁጣችንን ለማብረድ ፤ ህመማችንን ለመርሳት። በአትሌቲክስ ስፖርት አረንጓዴው ጎርፍን ለናፈቀ ህዝብ…በሪዮ ኦሊምፒክ እንቅልፍ አጥቶ ሀገሩን…ጀግኖች አትሌቶቹን ውጤት በስቃይ ሲከታተል ለሰነበተ ኢትዮጵያዊ…ኩራትም ሀፍረትም ለተላበሰ ወገን…ይህ ምላሽ ፈጽሞ አይገባውም። ፈጽሞ!
. ሀገርና ህዝብን ያላከበረ ሰብዕና በዶክተርነትም…በኢንጂነርነትም…በባለሀብትነትም…ማዕረግ ቢሸለም ከንቱ ነው! ምንም ነው! ምንም ታላቅነት…የኩራታችን ምንጭ የሆነው አትሌቲክሳችንን ለመምራት የሚያስችል አንዳች የሞራል ብቃትም አይኖረውም። ተስፋ አደርጋለሁ… አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስነ ምግባር እርምጃ እንደሚወስድ!