በባህር ዳር ፖሊሶች ሕዝቡ ከቤቱ ወጥቶ ስራ እንዲጀምር ሲያስገዱ ዋሉ።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ወያኔ ህዝቡ ከቤቱ እንዲወጣ በማስገደድ ላይ ዋሉ። የከተማዋን ባጃጆች በየማደሪያ ቦታቸው በመሄድ በግዳጅ ለማስወጣት እየሞከሩ ይገኛሉ፣ ስራ ካልጀመራችሁ 3000 ብር ትቀጣላችሁ በማለት ቢያስፈራሩም የስራ ማቆም አድማው እና የቤት ውስጥ ተቃውሞው ግን ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የተባባረ ህዝብ በባህር ዳር ታሪክ ይሰራል።ጭንቀት ውስጥ የሚኙት የወያኔ ፖሊሶች ባህርዳር በየቀበሌው እየዞሩ የቆሙ ተሽከርካሪወችን እንዲንቀሳቀሱ፤ በየመኪና ማሳደሪያ ሲያሥገድዱና ሲያሳድዱ ነው ያረፈዱት። ዛሬን ቀን ለሚሰሩ ባጃጆች በነፍስ ወከፍ ከ800 እስከ 1000 ብር በደህንነቶች አማካኝነት ቃል የገቡ ቢሆንም ህዝቡ ግን እንቢ ብሏል።