ውረድየ ውረድ የ * ከይትዋረድ የ ! * ሳትዋረድ * ውረድ – የዘንድሮ ኣሸንዳ ምርጥ ዘፈኖች !
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የዘንድሮ ኣሸንዳ ምርጥ ዘፈኖች !
±±±±±±±±±±

* ውረድየ ውረድ የ
* ከይትዋረድ የ !
* ሳትዋረድ
* ውረድ
፦ ዘፈኑ ሁለት ትርጉም ያለው ሲሆን ሰሙ ከበዓሉ የተያያዘ ቀጥታዊ ፍቺው ሳናዋርድህ ገንዘብ ልቀቅልን ሲሆን ወርቁ ደግሞ ህዝብ ሳያዋርድህ ስልጣን ልቀቅ የሚል ነው።
፦ ኣለሊየዮ ብኸብዱ
፦ ዳ ሙስና እዩ ዓዱ
፦ ለየሁት በሆዱ
፦ ሙስና ነው ልማዱ …!
; ሰሙ ከሙሰኞች ሰፈርእንደመጣ በሆዱ ቦርጭ ለየሁት የሚል ሲሆን ወርቁ ደግሞ ሙሰኛና ንፁህ ሰው ጠንቅቀን እናውቃለን እንደ ማለት ነው።
በሚናገሩት፣ በሚቀኙትና በሚዘፍኑት የሚናደድ ሰው ካለ “ኣታዮ ጉዳኛ
ጓለ ኣሸንዳ ዶ ኣለዋ ዳኛ”
ኣንተየው ጉደኛ
የኣሸንዳ ልጅ የላትም ዳኛ ብለው ስልጣናቸው ይገልፁለታል።
የኣሸንዳ ልጆች ለሶስት ቀናት በዘፍኑት፣ በሚናገሩትና ሚሰሩት ማንኛውም ስራ ተጣያቂ ነት የላቸውም።
ከህግ በላይ ናቸው። ይህ ባህል ከጥንት ጀምሮ የመጣ ልማድ ነው።
መልካም የኣሸንዳ በኣል !
