የአገሪቱን ህልውና ጥያቄ ውስጥ ሊከት የሚችል – የተቃውሞ ሠልፎቹ ፈርጀ ብዙ ሥጋቶች


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ሐምሌ 30 እና ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. በሁለቱ ትልልቅ የአገሪቱ ክልሎች የተከሰቱት የተቃውሞ ሠልፎች አካባቢያዊና የጋራ መነሻ ምክንያቶች እንዳሏቸው አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ፡፡ ለእነዚህ ችግሮች የአጭር ጊዜና ዘላቂ የሆኑ መፍትሔዎች የማይገኙ ከሆነ ተቃውሞው ሊቀጥልና የአገሪቱን ህልውናም ጥያቄ ውስጥ ሊከት የሚችል እንደሚሆን ያስጠነቅቃሉ፡፡ መንግሥት ችግሮቹን ሁሉ ለእሱ በሚመች መልኩ ብቻ በመተርጐምና የውጭ አካላትን ተጠያቂ በማድረግ ብቸኛው የመፍትሔ አካል እኔ ነኝ የሚለውን አቋም በመቀየር፣ የደረሰው ጉዳት ሳይባባስ ለማገገም ወደ ራሱ ማየት እንዲጀምር ያሳስባሉ፡፡ ለሞት፣ ለአካል ጉዳት፣ ለንብረት ውድመት፣ እንዲሁም ለእስራትና ለእንግልት እየዳረገ ያለው እንቅስቃሴና እየተሰጠ ያለው ምላሽ አድማሱን እንዳያሰፋና ሰላም እንዲፈጠርም ይጠይቃሉ፡፡ በተቃውሞ ሠልፎቹ ምክንያት የሚታዩ ፈርጀ ብዙ ሥጋቶች የጋራ መፍትሔ ይሻሉ ይላሉ፡፡ መንግሥት ለተቃውሞ ሠልፎቹ የሰጠውን ምላሽና የአስተያየት ሰጪዎችን ሐሳብ በተመለከተ ሰለሞን ጎሹ ያጠናቀረውን ዘገባ በፖለቲካ ገጽ ላይ ይመልከቱ፡፡   ዝርዝሩን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ፡፡