Camp111 የተባለ ኣዲስ የሜካናይዝድ ጦር ተቋቁሞ በቅማንቶች መሬት ላይ ሊሰፍር ነው።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Camp111 የተባለ ኣዲስ የሜካናይዝድ ጦር ተቋቁሞ በቅማንቶች መሬት ላይ ሊሰፍር ነው።
#Ethiopia #Amharaprotests #Gonder #Qimant #EPRDF #Tigray
Minilik Salsawi – mereja.com – ከሕወሓት ኣገዛዝ ወታደራዊ ደህንነቶች የሚደርሱ መረጃዎች እንደጠቆሙት ሕወሓት ከመከላከያ ሰራዊቱ ከሚሊሻዎችና ከቀድሞ የሕወሓት ታጋዮች የትግራይ ተወላጆችን በመመልመል ስልጣኑን የሚያስጠብቁለት የኣማራውን ሕዝብ ይመቱልኛል ያላቸውን ታማኝ ወታደሮች በኣንድ የሜካናይዝድ ጦር ስር በማሰባሰብ በቅማንቶች መሬት ላይ ግዙፍ ወታደራዊ ካምፕ111 በመገንባት ሊያሰፍር መሆኑን ተጠቁሟል።#ምንሊክሳልሳዊ

ዘረኛው የሕወሓት ኣገዛዝ የቅማንትን ሕዝብ መጠቀሚያ በማድረግ በጀግንነት
የሚኖረውን እና ቀልቡን የገፈፈለትን የኣማራን ሕዝብ ለመምታት ማሰቡ በራሱ ላይ መርዛም እባብ እየጠመጠመ ነው የሚሉት ኣደራጆቹ ወታደራዊ ደህንነቶቹ የቅማንት ሕዝብ በቅርቡ የሚያውቀውና የሚያምነው ኣማራን ነው ሲሉ ሕወሓት በገዛ እጁ ያሰፈራቸው የትግራይ ተወላጆች ሳይቀሩ ከፍተኛ ኣደጋ ውስጥ መሆናቸውን ሲጠቁሙ በኣሁኑ ወቅት ለም ከሆኑ የኣማራ መሬቶች በተለይ ከሰሜን ጎንደር ሕወሓት ያሰፈራቸውን ኣባላቶቹን እንዲያነሳ ከማይታወቅ ኣካል ማስጠንቀቂያ ደርሶታል።በኣጠቃላይ በኣማራ ክልል ውስጥ ወልቃይትን ጨምሮ የሰፈሩ የትግራይ ተወላጆች በከፍተኛ ኣደጋ ውስጥ በስጋት እየኖሩ ነው ሲሉ ምጮቹ ይናገራሉ፥ ሕወሓት ያለው እድል ሕዝቡን ካአደጋና ከስጋት ለማላቀቅ ኣንድም ኣከባቢውን ለነጠቀው የወልቃይት ሕዝብ ማስረከብ እና ለቆ መውጣት ኣሊያም ሕዝቦች እንደድሯቸው ተፈቃቅረና ተከባብረው እንዲኖሩ ነጻነታቸውን ማክበር ያስፈልጋል፤የሰሜን ጎንደር ሕዝብ መሬቱን ተነጥቆ እንዲሁ እንደማይኖር ሁሉ መሳሪያን ለማስፈታት ማሰብ ወደባሰ የእርስ በርስ ጦርነት መግባት ነው ሲሉ ምንጮቹ ተናግረዋል።#ምንሊክሳልሳዊ