አማራን “ለሃጫም” ብሎ የተሳደበው የብአዴን ስ/አ ኮሚቴ አባል አለምነው መኮንን ደሴ ከተማ ውስጥ ድብደባ ደረሰበት
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የብአዴን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆነውና አማራን ህዝብ “ለሃጫም” እያለ የሚሳደበው አለምነው መኮንን በትላንትናው እለት ወሎ ውስጥ በደሴ ከተማ ላሊበላ ሆቴል አካባቢ ማንነቱን ያወቁ የከተማው ነዋሪዎች ድንጋይ ወርውረውበታል። በሁኔታው የተደናገጠው የወያኔ ቅጥረኛ መኪናው ውስጥ ሮጦ ከገባ በኋላ በታጣቂዎች ታጅቦ ሊያመልጥ ችሏል።
አለምነው መኮንን፣ ገነት ዘውዴ፣ ታደሰ ካሥና ሌሎችም የብአዴን አመራር አባላት ላለፉት ሶስት ቀናት ወሎ የሚገኙ የድርጅቱን ካድሬዎች ሰብስበው ከህወሃት የተሰጣቸውን ትእዛዝ ለማስፈጸም ደፋ ቀና በማለት ላይ ይገኛሉ። ከተሰጣቸው ትእዛዝ አንዱ በደሴና አካባቢው የአማራ ፖሊስ አባላትን ትጥቅ ማስፈታት ነው።