የጎጃም እና የሸዋ የዛሬ ዉሎው (ነሐሴ 5)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የፊታችን እሁድ ነሐሴ 8 ቀን 2008 ዓ.ም በሸዋ፣ ከባህር ዳር ዉጭ ባሉ የጎጃም ከተሞች፣ በሰሜን ሸዋ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳም በአልጃዚራ ቀርቦ አንድ የተናገረው ነገር አለ። ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት አለው ነው ያለው። ሕገ መንግስቱን በግልጽ ዜጎች ሰልፍ የማድረግ መብት እንዳላቸው ያረጋግጣል።
ሆኖም ግን ሕወሃቶች በአደባባይ የሚናገሩት እና በተግባር የሚያደረጉት ነገር የተለያየ ነው። እርስ በርሱ የሚቃረን። ለዚህ ነው ኢትዮጵያዉን ድምጻችንን እናሰማ ብለው ሲንቀሳቀሱ እነርሱ ደግሞ በተጻራሪው የሕዝብን ድምጽ ለማፈን ደፋ ቀና እያሉ ነው።በወሎ ያለውን ሁኔታና ምን ያህል ሕዝቡን እያዋከቢት እንደሆነ የሚገልጽ የተለያዩ ዘገባው እንደሚከተው ቀርበዋል፡
====================
# ሰበርዜና
ድሮም # የደብረማርቆስ ልጆች # ምሽግ # ሰባሪ ናቸው። በውስጥ መስመር አሁን የደረሰን ትክክለኛ የአይን ምስክር መረጃ አስር እሚሆኑ የደብረ ማርቆስ ልጆች አባይ በርሃን ተሻግረው አባይ በርሃ መውጫ ላይ ጒፂዎን እምትባል ከተማ ሳይደርስ ማምሻውን ከ1፡20 እስከ 1:50 በቆየ ፍልሚያ 30 አጋዚ ወታደር ገለው የአጋዚዎችን መኪና አጋይተው እኛ
ማርቆሴዎች የተክልየ ዘር እያሉ እየፎከሩ ወደ በርሃው ማምሻውን ገብተዋል። የአይን እማኞች እንዳሉት የተረፈ አጋዚ ወታደር እንደሌለ እና የከተማይቱ መብራት በተኩሱ ልውውጥ ጠፍቷል። አሁን ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ ከፍቼ ኩማንዶ አምስት ኦራል አጋዚ አካባቢውን ወሮታል። ጎጃም ዝም ሲል እንጂ ካፈረ መመለሻ የለውም።
#ደብረማርቆስ!!
ከአካባቢዉ በደረሰኝ መረጃ መሰረት ደብረ ማርቆስ እጅግ ተወጥራለች። ከደብረማርቆስ ዙሪያ ወረዳወች የአካባቢዉ ሚሊሻወች ተመርጠዉ ሰላማዊ ሰልፉን ለመቆጣጠር ተመድበዋል።በሰሞኑ በነበረዉ ስብሰባ የአካባቢዉ ሚሊሻወች ወደ ህዝብ ላይተኩሱ እርስ በርስ ተስማምተዋል። ይሄን ለመስበር ወያኔ የዶለተዉ እነዚህን የአካባቢዉ ሚሊሻወች ሲቪል ልብስ በማልበስ እና ከአጋዚ ፊት በማድረግ እርምጃ የማይወስዱ ከሆነ አጋዚ በአካባቢዉ ሚሊሻወች እርምጃ እንዲወስድ የሚል ነው ።ለዚህም የአካባቢዉ ሚሊሻወች ለመልሶ ማጥቃት ተዘጋጅተዋል። የበላይ ዘለቀ የመንፈስ ልጅ አጋዚን አባይ በረሃ ላይ የእሳት ራት ማድረግ ግድ ይልሃል!!!!
#ደብረ_ብርሃን
ደብረ ብርሃን ህውሀት ኢህአዲግ በግዴታ የከተማውን ወጣቶችና የህዝብ ትራንስፓርት አገልግሎት ሰጪ ሹፌሮችን ተሰብሰቡ በማለት በማስገደድ ላይ መሆናቸውና የትራንስፓርት አገልግሎት መቆሙን በቦታው ያሉ ወጣቶች በፎቶ አስደግፈው ልከውልኛል በተለይ በቅዳሜና በእሁድ የሚደረጉ ሰልፎች ያስጨነቁት ገዤው ስርአት በቀጣይ ቅዳሜና እሁድ ህዝብ ወደ አደባባይ እንዳይወጣ ማስፈራራት ላይ መሆናቸውና ህዝብ በትራንስፓርት እጦት በመንገላታት ላይ መሆኑንም አልሸሸጉኝም ።
ድል ለሰፊው ህዝብ