የወሎው የዛሬ ዉሎ (ነሐሴ 5)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የፊታችን እሁድ ነሐሴ 8 ቀን 2008 ዓ.ም በሸዋ፣ ከባህር ዳር ዉጭ ባሉ የጎጃም ከተሞች፣ በሰሜን ሸዋ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳም በአልጃዚራ ቀርቦ አንድ የተናገረው ነገር አለ። ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት አለው ነው ያለው። ሕገ መንግስቱን በግልጽ ዜጎች ሰልፍ የማድረግ መብት እንዳላቸው ያረጋግጣል።
ሆኖም ግን ሕወሃቶች በአደባባይ የሚናገሩት እና በተግባር የሚያደረጉት ነገር የተለያየ ነው። እርስ በርሱ የሚቃረን። ለዚህ ነው ኢትዮጵያዉን ድምጻችንን እናሰማ ብለው ሲንቀሳቀሱ እነርሱ ደግሞ በተጻራሪው የሕዝብን ድምጽ ለማፈን ደፋ ቀና እያሉ ነው።
በወሎ ያለውን ሁኔታና ምን ያህል ሕዝቡን እያዋከቢት እንደሆነ የሚገልጽ የተለያዩ ዘገባው እንደሚከተው ቀርበዋል፡
==================
ወልዲያ/መርሳ፤ ዛሬ ወያኔዎች ከወልደያ ከተማ 30 ኪሎ ሜትር ያከል በምትርቀው በመርሳ ከተማ ‹‹እርዳታ እንስጣችሁ!›› በሚል በከተማዋ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዐማሮችን ሰብስበው ነበር፡፡ ሆኖም ለእርዳታ የተሰባሰቡት ነዋሪዎች ‹‹ወልቃይት የዐማራ አይደለም!›› የሚል መፈክር ይዘው እንዲወጡ ያን ካላደረጉ ግን እርዳታው እንዳማይሰጣቸው ተነግሯቸዋል፡፡ የመርሳ ዐማሮች ግን ‹‹ድኅነታችን ይሻለናል›› በማለት ከመላው የዐማራ ሕዝብ ጎን መሰለፋቸውን አስመስክረዋል፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በወልድያ ከተማ የባጃጅ ሾፌሮችን የከተማ አስተዳደሩ ሰብስቦ በሳምንቱ መጨረሻ በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይወጡ ወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄንም እንዲያወግዙ መልእክት ተላልፎ ነበር፡፡ ሆኖም እስከ አንድ ሺህ የሚጠጉ የስብሰባ ተሳታፊዎች ከወገኖቻችን ጋር ነን በማለት ስብሰባ ረግጠው መውጣታቸው ተሰምቷል፡፡
በተያያዘም በደቡብና በሰሜን ወሎ ዞኖች የሚታሰሩ ወጣቶች ተበራክተዋል፡፡ ከቀናት በፊት ከሐይቅ ከተማ የታሰረው ወጣት እስካአጽናፍ እስካሁን ያልተፈታ ሲሆን በሀብሩ ወረዳ ነዋሪ የሆነው ወጣት ናትናኤል ሰኢድ ከቀናት በፊት ታፍኖ የደረሰበትም እንደማይታወቅ ዛሬ የደረሰን መረጃ ያመለክታል (ፎቶው ተያይዟል)፡፡
=====================
☞ በሰሜን ወሎ ዞን በላሊበላ ከተማና አጎራባች የገጠር ከተሞች ወጣቶችን በቀንና በለሊት የማፈኑ ሂደት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ትላንትና ከኩልመስክና ከላሊበላ ከተማ አስር ወጣቶች ታፍነው የተወሰዱ መሆኑንና አንድ የቀድሞ የቅንጅት አባል የነበረና “አለምዬ ሶራ” የተሠኘው ባህላዊ የሙዚቃ ክሊፕ ላይ በተወዛዋዥነት የተሳተፈው ስሙ ያልተገለፀ ወጣት ለሊቱን በመንግስት ሀይሎች ከመኖሪያ ቤቱ ታፍኖ እንደተወሠደ ከደቂቃዎች በፊት ከስፍራው በውስጥ መልዕክት መቀበያ የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል፡፡ ገዢው መንግስት ከህዝብ የተነሳበትን ከረር ያለ ተቃውሞ ለመቀልበስ እንደመፍትሄ የወሰደው ዜጎችን የመግደልና የማሰር አረመኔያዊ ተግባሩን በሌሎች አካባቢዎችም አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
====================
<< የህዝቡን ቁጣ ልታዘገዩት እንኳ ብትችሉ ፈፅሞ ግን አታቆሙትም፡፡ የሞቱት እኮ የኛም ወገኖቻችን ናቸው፡፡>>
.
ዛሬ በኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ የተመራው የአሽከርካሪዎች መድረክ ባለመግባባት ተጠናቀቀ፡፡ ከመድረኩ የተሠጠውን እድል ተጠቅመው ያለአንዳች ፍርሀት ስሜታቸውን ሲገልፁ የዋሉት ተሳታፊዎች፣ ከክልል ለመጡት የስራ ሀላፊዎችና ለመድረክ መሪው ከንቲባ ፈተና ሁነው አልፈዋል፡፡ << እናንተ ችግርን ማዳመጥ እንጂ መፍታት አታውቁም>> ፣ << በሙስናና ብልሹ አሰራር የተጨማለቀው ስርአት ህዝቡ ትዝ የሚለው አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባ ብቻ ነው፡፡>> የሚል ሀሳብ የሠነዘሩት ተሳታፊዎች ፣ በመድረኩ ላይ የኦሎምፒክ ዋና ተሳታፊው ሮቤል ኪሮስን ሀገሪቱ ላለችበት የአንድ ብሄር የበላይነትና ዘረኝነት የተጠናወተው ብልሹ አሰራር በምሳሌነት አቅርበዋል፡፡ << ለህዝብ ሰላማዊ ጥያቄ ምላሹ ጠብመንጃ መሆኑ ህዝባዊ እንቢተኝቱን ያባብሰዋል እንጂ አያስቆመውም>> ያሉት ተሳታፊዎች << አሁንም ቢሆን የህዝብ ቁጣ ባየለበት ሁኔታ የሀይማኖት አባትና የሀገር ሽማግሌ እየሰበሰባችሁ ቁጣውን ለማብረድ የምታረጉት ጥረት ፣ ህዝባዊ እንቢተኝነቱን ያዘገየው እንደሆነ እንጂ ፈፅሞ አያስቆመውም፣ የፈሰሰው ደም እኮ የወገኖቻችን ነው፡፡ >> ሲሉ አቋማቸውን አንፀባርቀዋል፡፡
#Amharaprotests
#ኮምቦልቻ
.
የወያኔ ካድሬዎች የከተማዋን የታክሲና ባጃጅ ሹፈሮች በአስገዳጅ ሁኔታ ሰብስበው ፣ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ እንቢተኝነት ዙሪያ እያወያዩ ሲሆን፣ አብዛሀኞቹ አሽከርካሪዎች ግን የመጣውን እንቀበላለን በማለት በመድረኩ ሳይገኙ ቀርተዋል፡፡