ህወሃት ኢህአዴግ በኦሮሚያ ክልልና በአማራ ክልል በገጠመው ውጥረት በአፋር ክልል በሎጊያ የግዳጅ ሰልፍ እንዲካሄድ አደረገ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ቢቢኤን ፦ በዛሬው እለት በአፋር ክልል በሎግያ ከተማ በኦሮሚያ ና በአማራ እየተከሔደ ያለው ተቃውሞ እኛን አይወክለንም ብላችሁ ሰልፍ እንዲወጡ ማህበረሰቡ ከቤቱ እንዲወጣ ና ለባለባጃጆች ስራ አቁመው ባጃጁ ሰልፍ ቦታ ላይ ይ ዞ እንዲገኝ በግዳጅ ሰለፍ እንዲወጡ ተደርጓል።
ከ100 ባላነሱ በክልሉ ልዩ ሃይል በማስፈራራት በሎግያ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ሰልፍ እንዲካሄድ ተደርጓል አንደንድ ሰዎች የመጡበት አላማ የማያውቁም እንዳለ ተናግረዋል በቦታው ላይ የተገኙት ቁጥራቸው አነስተኛ ተገደው እንደወጡ ለቢቢኤን የገለፁ ሲሆን የአፋር ህዝብ ከኦሮሞና ከአማራ ወገኖቹ ጎን እንደሆነ ገልፀዋል። እነዚህን የግዳጅ ሰልፎች በመንግስት ሚዲያ የሚመለከት ሰው የመንግስትን ርስበርስ የማፋጀት ሴራ እንዲረዳ ሲሉ የአፋር ምንጮቻችን አያይዘው ገልፀዋል።
በአሳይታም ተመሳሳይ የግዳጅ ሰልፍ ለማድረግ እያስገደዱ መሆናቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል በወሎ መንግስትን በመቃወም ሰልፍ ለማድረግ ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የቢቢኤን ምንጮች ገልፀዋል