አዘዞ ዉስጥ ከፍተኛ ዉጊያ እየተደረገ ነዉ።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አዘዞ ዉስጥ ከፍተኛ ዉጊያ እየተደረገ ነዉ።
የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችን ጥሪን ሰምቶ ትጥቁን ይዞ ወደ ጎንደር ላይ በመገስገስ የነበረዉ የአዘዞና የ አካባቢዉ ነዋሪ ከትግራይ መጥቶ ከሰፍረ ልዩ ጦር ጋር እየተዋደቀ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል። እስከ አሁን ድረስ ከሁለቱም ወገን ያለዉ ጉዳት በይፋ አልታወቀም። በጎንደር ዉስጥ በተለያዩ ከተሞች ያለዉ ነዋሪና በገጠር ያለዉ አርሶ አደር በጣሙን የታጠቀ በመሆኑ ከትግራይ መጥቶ ለሰፈረዉ ጦር ነገሮች ቀላል እንደማይሆኑ የቢቢኤን የጎንደር ምንጮች ገልጸዋል።
ዛሬ የኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱን ፍርድ ቤት መቅረብ ተከትሎ የጎንደር ህዝብ በፍርድ ቤቱ ዙሪያ በመሰብሰብ በሰላማዊ መንገድ ድምጹን ያሰማ እንደነበር አይዘነጋም። ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱን ወደ ማእከላዊ ለመዉሰድ የሚደረገዉን ጥረት ለማክሸፍና የታሰሩት የወልቃኢት ህዝብ ተወካዮች እንዲፈቱ የጎንደር ህዝብ በሰላማዊ መንገድ ቢጠይቅም፤ ጎንደር የከተሙት የህወሃት የጦር ሰራዊት አባላት በሰላማዊ ሰዉ ላይ ተኩስ መክፈታቸዉን የቢቢኤን የጎንደር ምንጮች አሳዉቀዋል።
ቢቢኤን እስከ አሁን ባገኘዉ መረጃ ሶስት ሰዎች በጎንደር ዉስጥ የሞቱ ሲሆን፤ ቁጥሩ ሊያሻቅብ ይችላል የሚልም ስጋት አለ። አደባባይ የወጣዉ የጎንደር ህዝብ መፈክሮችን እያሰማ በዘመነ ኢህአዴግ የመጣዉን ባለ ኮኮብ ባንዲራ አዉርዶ ኮኮብ የለሽ ባንዲራ ማዉለብለቡ ታዉቋል። ጎንደር ከዉጥረትም ባሻገር ጦርነት ዉስጥ ናት ሲሉ የቢቢኤን ምንጮች እየገለጹ ነዉ። የጎንደሩ ጦርነት ወዴት እንደሚያመራ ባይታወቀም ህዝቡ “በቃኝ!እምቢኝ!አሻፈረኝ!” ብሎ መነሳቱን ለማወቅ ተችሏል።