ጎንደር ስልክና ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል፤ ማክሰኝት የመለስ ቢል ቦርድ ተቃጥሏል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ጎንደር ስልክና ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል፤ ማክሰኝት የመለስ ቢል ቦርድ ተቃጥሏል
– ደብረታቦር ጠዋት 12 ሰአት ጀምሮ የተጋድሎ ሰልፍ ይደረጋል
– ደብረታቦር ወገኖቻቸውን በስለላ አሳልፈው የሚሰጡ ባንዳዎች አርፈው እንዲቀመጡ መልእክት ደርሷል፤ ስም ዝርዝራቸውና ፎቷቸው ከታች ቀርቧል፡፡Muluken Tesfaw
ከጎንደር ከተማ 40 ኪሎ ሜትር ማክሰኝት ድረስ ዐማራው ተጋድሎውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በማክሰኝት ከተማ ዐማሮች ገንፍለው ወጥተው በምሽት ተጋድሏውን ቀጥለዋል፡፡ የመለስ ፎቶን የያዘ ቢል ቦርድ ተቃጥሏል፡፡ ወደ ጎንደር ለእርዳታ እየፈጠኑ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ሆኖም በጎንደር የወያኔ ጦር ከንጹሐን ዐማሮች ላይ የለየለትን ጦርነት ካወጀ ከሰአታት በኋላ ስልክና ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ተቋርጧል፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ስልክ የሚሠራ የነበረ ቢሆንም አሁን ሙሉ በሙሉ ከመረጃ ምንጮቻችን ጋር ግንኙነታችን ተቋርጧል፡፡ ይህን መልእክት የሚያነብ የዐማራ ሕዝብ እልቂት የሚያሳስበው ወገን ሁሉ በውስጥ መስመር የሚያገኘውን መረጃ እንዲያቀብል በዚሁ አጋጣሚ እንጠይቃለን፡፡ ከአርማጭሆና ከቋራ አካባቢ ወገኖቻቸውን የሚታደጉ ዜጎች እየመጡ መሆናቸውን ብንሰማም ወደ ከተማ ስለመግባታቸው ግን የታወቀ ነገር የለም፡፡


ይህ በዚህ እንዳለ በደብረታቦር ከተማ ነገ ቅዳሜ ሐምሌ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. የሚደረገው የዐማራ ተጋድሎ ሰልፍ ሙሉ በሙሉ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡ የተጋድሎ ሰልፉ ጠዋት ቴዎድሮስ አደባባይ ከጠዋቱ 12 ሰአት ይጀመራል፡፡ የአባቶቻችን ደም የፈሰሰባት ሰንደቅ ዓላማ በበቂ መጠን ተዘጋጅቷል፡፡ የመፈክር ባነሮች ከአንድ ቀን በፊት ቀድም ብለው ታትመዋል፡፡ ነገ በደብረታቦር ከአንድ መቶ ሽህ በላይ ሕዝብ የተጋድሎ ሰልፍ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የሚከተሉት በከተማዋ የሚኖሩ አንዳንድ ባለሀብቶችና የመንግሥት ሠራተኞች ወጣቶችን አሳልፈው በመሥጠት ማስቸገራቸው ታውቋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘረው ግለሰቦች ቤተሰብ የሆናችሁ አርፈው እንዲቀመጡና ከወገኖቻቸው ጎን እንዲሆኑ መምከር አለባችሁ፡፡
1. አቶ በሪሁን የመካለከያ ሠራዊት ምልስና የደቡብ ጎንደር ዞን ብአዴን ኃላፊ ሲሆን የአካባቢውን ወጣቶች እንዳስመረረ ነው ጥቆማዎች የሚደርሱን፡፡
2. አቶ ግርማቸው አባተ፡ አቶ ግርማቸው አባተ ከጥቂት ዓመታት በፊት ከጎንደር ዩንቨርሲቲ ትምህርቱን አጠናቆ አሁን የደብረታቦር ወጣቶችን እያሳደነ ያለ ግለሰብ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ አቶ ግርማቸው ‹‹አገልግል›› የተባለ የባሕል ምሽት ዘወትር የሚያመሽ ግለሰብ ሲሆን የተጣለውን ሳይቀር ለወያኔ አሳልፎ የሚሠጥ ባንዳ ነው፡፡ በዚሁ አጋጣሚ የአገልግል የባሕል ምሽት አቶ ግርማቸውን የመሠሉ ወያኔ አደሮች የሚያስያስተናግድ ከሆነ ከዚህ ቤትም ባለመጠቀም የንግድ ተቋሙን ማዘጋት ያስፈልጋል፡፡
3. አቶ ታደሰ አደመ፡ በኮንስትራክሽን ሙያ የተሰማራ
4. አቶ ኤርሚያስ አደመ፡
እነዚህ ግለሰቦች የከተማዋን ወጣቶች የሚያሳፍሱና የወያኔ ተላላኪ ግበረ አበሮች ናቸው፡፡ ከእዚህ እኩይ ሥራቸው እንዲታቀቡ ደጋግመን እናስጠነቅቃለን፡፡

Muluken Tesfaw's photo.
Muluken Tesfaw's photo.
Muluken Tesfaw's photo.
Muluken Tesfaw's photo.