በቅድስት አገር እየሩሳሌም የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የህወሃት ያበላሽውን ሰንደቅ ዓላማ አወርደው በምትኩ ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አውለበለቡ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በእየሩሳሌም ከተማ ውስጥ የሚገኘው ታላቁ የደብረ ገነት ኪዳነ ምሕረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዕድሜው ከ100 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን፣ በሽዎች ለሚቆጠሩ ምዕመናን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ባለፈው ዕሁድ በጎንደር ከተማ የተደረገውን ከ800,000 ሽህ በላይ ህዝብ የተሳተፈበት ታሪካዊ ትዕይንተ ሕዝብ ተከትሎ በእየሩሳሌም ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወያኔ የምዕመናንን የዕምነት ነጻነት በመጻረርና በሐይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ቤተክርስቲያን መግቢያ ላይ የተከለውን አወርደው ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አውለብልበዋል። ይህም ለኪዳነ ምሕረት የአስራት አገር ሆና የተሰጠችው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በደብረ ገነት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ውስጥ መውለብለብ በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ይኸው ሰንደቅ አላማ እንደሚውለበለብና የኢትዮጵያ ትንሳዔ መምጣቱን የሚያረጋግጥ ነው የሚሉ በርካታ ኢትዮጵያዊያን አሉ። ሁላችንንም ኢትዮጵያዊያንን የአገራችንን ትንሳዔ ለማየት ያብቃን።
https://www.youtube.com/watch?v=Phy_MXHQ2RY