በጎንደር ሰልፍ ላይ ከፍተኛ የሆነ ውጤት መመዝገቡን ከሰልፉ ኣስተባባሪዎች የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በጎንደር ሰልፍ ላይ ከፍተኛ የሆነ ውጤት መመዝገቡን ከሰልፉ ኣስተባባሪዎች የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል – Minilik Salsawi

የወልቃይት ኮሚቴዎች ቢታሰሩም በምትካቸው ሙሉ ኮሚቴ ተቋቁሟል።የጎንደር ሕዝብ ሰልፍ በየወረዳው ይደገማል። በጎንደር ሰልፍ ላይ ከፍተኛ የሆነ ውጤት መመዝገቡን ከሰልፉ ኣስተባባሪዎች የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል፤በዚህም መሰረት በወልቃይት ኮሚቴዎች ምትክ ሙሉ ምትክ ኮሚቴዎች የተዋቀሩ ሲሆን ትግሉን ለመቀጠል በየኣማራ ክልል ከተማዎችና ወረዳዎች ኣስፈላጊዉን ኔትወርክ ያደራጁ ቡድኖች በወጣቶች እንዲገነቡ ኣስፈላጊዉን መስመር ከግብ ለማድረስ ኮሚቴ ተቋቁማል፤የታሰሩ የወልቃይት ኮሚቴዎችን ለማስፈታት ኣስፈላጊው መስዋትነት ሁሉ ይከፈላል ሲሉ ሰልፈኞቹ ተናግረዋል። የጎንደር ሕዝብ ሰልፍ በየወረዳው ይደገማል። ሕዝቡ በፍጹም ኣያቆምም።የኣማራ ክልል ከተሞች ሁሉ በኣደረጃጀት ታቅፈው ትልቅ ስራ እየተሰራ ነው።

የኢሕ አዴግ ኣመራሮች ከሕወሓት በስተቀር የሕዝቡን ጥያቄ ደግፈውታል፥ ከኣማራ ክልል ውጪ የመጡ ወታደሮች በፍርሃት ተውጠው ነበር።የክልሉ ፖሊስና ሚሊሻ ከሕዝቡ ጎን ተሰልፈው ነበር።የኣማራ ገበሬዎች በተለይ ቆለኛው በጎንደር ሰልፍ ኣንድ ችግር ቢነሳ ካልምንም ቅድመ ሁኔታ የሕወሓትን ወታደሮች ይመታል የሚል ስጋት በወያኔ ኣገዛዝ ኣድሮ ነበር፥ ወያኔ ያሰፈረው ጦር ሰልፉን ከተቀላቀሉት በኣማራ ክልል ፖሊስ እና ከታጠቀው ሕዝብ ሚሊሻውን ጨምሮ ጋር ሲወዳደር ከቁጥር ኣይገባም ነበር ።