ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆን የአማራ ሕዝብ እሁድ ሐምሌ 25 ቀን 2008 በጎንደር ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣል፤ በባህር ዳር፣ ደሴና ደብረ ብርሃን ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
- ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆን የዐማራ ሕዝብ እሁድ በጎንደር ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣል
- በባህር ዳር፣ ደሴና ደብረ ብርሃን ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል
#Ethiopia #AmharaProtests #Gonder #MulukenTesfaw #MinilikSalsawi በወልቃይት የዐማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴዎች ላይ የሚደርሰውን አፈናና ግድያ እንዲቆም የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ እሁድ ሐምሌ 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ለማካሔድ የአገር ሽማግሌዎችና የሕዝብ ተወካዮች ለከተማ አስተዳደሩ ጥያቄ አቅርበ መላው አማራ ታሪካዊ ሰልፍ ያደርጋል ፡፡ነገ እሁድ ሐምሌ 17 ቀን 2008 ዓ.ም. ጎንደር ላይ ሲካሄድ ታስቦ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ወደሚቀጥለው ሳምንት ማለት ወደ ሐምሌ 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ተዛውሯል። ሰልፉ በአንድ ሳምንት የተራዘመው በጎንደር ዙሪያና በሌሎች የአገራችን አካባቢዎች የሚኖሩ አማሮች ወደ ጎንደር ከተማ ይተሙ ዘንድ ጊዜ በማስፈለጉ ነው። ስለዚህ ነገር እሁድ ሐምሌ 17 ቀን 2008 ዓ.ም ጎንደር ላይ ሰልፍ የለም። በሚቀጥለው ሳምንት እሁድ ግን በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ መላው አማራ ታሪካዊ ሰልፍ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
እሁድ ዐማሮች በሚያደርጉት ሰላማዊ ሰልፍ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ እንደሚወጣ ብሎም በሕወሓት የሚደርሰውን አፈናና ግድያ እንደሚያወግዝ ሲሆን በጎንደር ታሪክ ታላቁ ሰላማዊ ሰልፍ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የዐማራው ሕዝብ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ የሚያደርገውን ሰልፍ በሰርጎ ገብ የወያኔ ሰዎች ችግር እንዳይፈጠርም ጥንቃቄ ተደርጓል ተብሏል፡፡ በጎንደር የተጠየቀው የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ በምንም መልኩ ሊከለከል እንደማይችል አዘጋጆች አክለው ገልፀዋል፡፡
“የከተማ አስተዳደሩ በሕወሓት ጫና ሰላማዊ ሰልፉን ፈቃድ ቢከለክልስ ምን ዋስትና አላችሁ” በማለት ለሰልፍ አዘጋጆች ላቀረብንላቸው ጥያቄ “እኛ የጠየቅነው ሰላማዊ ሰልፍ ነው፤ የከተማ አስተዳደሩ ሕወሓትን በመፍራት ሕዝቡን ይከለክላል የሚል እምነት የለንም፤ ካደረገው ግን ሥርዓት አልበኝነትን እንዲነግሥ ይሻል ማለት ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በባህር ዳር፣ ደሴና ደብረ ብርሃን ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ኮሚቴዎች ተመርጠው እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተያያዘ በጎንደር የሚገኘውን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ ወደ ማዕከላዊ ተወስደው ከባድ የወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ያሉትን የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢዎች እንዲፈቱ የሚጠይቁ የዐማራ አመራሮች መበራከታቸው ታውቋል፡፡ ወደ ማዕከላዊ የተወሰዱት የጥያቄ አቅራቢው አባላትና የወልቃይት አማራ ተወላጆች በቤተሰቦቻቸው ለመጠየቅ ቢሄዱን እስካሁን አልተፈቀደላቸውም፡፡
