በኬንያ ናይሮቢ ኢትዮጵያ ኤምባሲ የወያኔ የደህንነት ኣባላት ሚስጥራዊ ስብሰባ ተደርገ።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በኬንያ ናይሮቢ ኢትዮጵያ ኤምባሲ የወያኔ የደህንነት ኣባላት ስብሰባ ተደርገ።
በኬንያ የወያኔ ኤምባሲ ጽ\ቤት የሕወሓት ሰዎችንና በስደተኛው ውስጥ ገብተው የሚሰልሉ የወያኔ ደህንነት ኣባላትን ያካተተ ስብሰባ ተካሂዷል።በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተደረገ ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ በጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ለደህነቶች ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው ::
በትላንትናው እለት ማለትም ሐምሌ 13 ቀን 2008 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኤምባሲ በተደረገው እና ሙሉ ቀን በፈጀው ሚስጥራዊ የደህንነት አባላት ስብሰባ በኬንያ እንዲሰሩ የተመደቡ የደህንነት አባላት ስራቸውን በአግባቡ እየተወጡ ባለመሆኑ በስራ ላይ መዝረክረክ እያሳዩ በመሆን እና ክትትሉ በመላላቱ ናይሮቢን መናህሪያቸው ያደረጉ ጋዜጠኞች እና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የመንግስትን እና የሀገሪቱን ገፅታ ለማበላሸት ከአለማቀፍ ተቅዋማት ጋር ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ ከመሆኑም ባሻገር በሀገር ውስጥ የሚደረጉ እና ጸረ ሰላም ሀይሎች የሚፈጥሩዋቸውን እና እያደረጉ ያሉትን እንቅስቃሴዎች በማጋጋል እና የመረጃ ልውውጦችን እያደረጉ ሀገሪቱ ወደማያባራ ቀውስ ውስጥ እንድትገባ እያደረጉ በመሆኑ በአስቸኩዋይ እርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚል መመሪያ መተላለፉን ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ በስብሰባው ላይ ተካፋይ የነበሩ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡እንደምንጮቻችን ገለፃ የመጀመሪያው ትኩረት እንዲደረግባቸው ተብሎ ከተቀመጡት በቅርቡ በሌለበት በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብሎ የተወሰነበት ጋዜጠኛ ግዛው እና በአምነስቲ ኢንተርናሽናል ርሃብ አድማ ያደረጉ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ከስብሰባው ተሳታፊዎች የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ከኢትዮጵያ ሸሽተው የመጡ ፓለቲከኛና ጋዜጠኞች በነፃነት በኬንያ ውስጥ ተደራጅተውና ማህበር መስርተው ሲንቀሳቀሱ የተሰጣችሁን ተልኮ አልፈፀማችሁም በማለት በናይሮቢ የሚገኙ የወያኔ ሰላዮች በኣለቆቻቸው ተወቅሰዋል። የተሰጣችሁን ተልእኮ በተግባር ኣልተወጣችሁም በማለት ከፍተኛ ቁጣ ወርዶባቸዋል::
በተጨማሪ በኬንያ ናይሮቢ የሚኖሩ ስደተኞች አምስቲ ኢንተርናሽናል የርሃብ አድማ በማለትና የሀገሪቱን የፓለቲካ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በማህበራዊ ድህረገጾች ንቁ ተሳታፊ ሆነው ተቃዋሚ ስደተኞች ሲጠናከሩ ሰላዮቹ ፈዘዋል በሚል ተወርፈዋል። የግለሰቦችን ስም እየጠቀሱ መፍትሄ ያሉትን ሲመክሩና ሲወያዬ መዋላቸውን ምንጮች ገልፀዋል የእያንዳንዱ ተቃዋሚ ስደተኛ ኣዋውል እና እንቅስቃሲ እንዲጠና በተለይ ጋዜጠኛ ግዛውን የወያኔ ሰላዮችና ተላላኪዋች ክትትል አንዲያደርጉበት ያለበትን ቦታ ጥናት ማድረግ እንዳለባቸውና ቀጣይ ከዚህ በኋላ ወደ ስራ እንዲገቡ የስራ መመሪያ እንደተላለፈላቸው በስብሰባው ላይ ከተሳተፉ ምንጮች ለመረዳት ተችሏል።