ጥቅማቸው የተነካና የደነገጡ የሕወሓት ኣባላትና ደጋፊዎች የሆኑ የትግራይ ምሁራን ስለ ኢትዮጵያ የፓናል ውይይት ለሃምሌ16 ጠርተዋል።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
#Ethiopia ጥቅማቸው የተነካና የደነገጡ የሕወሓት ኣባላትና ደጋፊዎች የሆኑ የትግራይ ምሁራን ስለ ኢትዮጵያ የፓናል ውይይት ለሃምሌ16 ጠርተዋል። በሃረርጌና በሸዋ የተነሳው የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። #OromoProtests #Amharaprotests #TPLF #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ትላንትና ያገረሸው በምእራብ ሸዋ የተቀሰቀሰው የሕዝብ ተቃውሞ ዛርዐም በጀልዱ ወረዳና በዙሪያ ባሉ ከተሞች ቀጥሎ መዋሉ ከኣከባቢው የተገኘ መረጃ ያሳያል፥ የወያኔ ሰራዊት ኣባላት ከከባድ መሳሪያዎቻቸው ጋር በቦታው መድረሳቸው የታወቀ ሲሆን የኢንተርንት ኣገልግሎት መቋረጡ ታውቋል።
በተጨማሪ በምእራብ ሃረርጌ በኣሰቦት ከተማ በተነሳው ተቃውሞ በርካታ ሰዎች ተይዘው ሲታሰሩ በኣከባቢው የተሰማራው የወያነ ኣግዓዚ ሰራዊት ወደ ሕዝቡ በመተኮስ ላይ እንደነበር የገለጹት ምንጮች በሃረርጌ በዴሳ ከተማም ተቃውሞ የተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሃገሪቱ የተነሳውን የሕዝብ ተቃውሞ እንቅልፍ የነሳቸው የሕወሓት ደጋፊዎች እና ኣባላት ሃምሌ 16 2008 በጣሊያ ካልቸራል ኢንስቲቲዩት የፓናል ውይይት ማዘጋጀታቸው ታውቋል፥የሕዝቡ አንቅስቃሴ በተለይ በኣማራው ክልል የተነሳው ተቃውሞ ኣስደንጋጭ የሆነባቸው የሕወሓት ደጋፊዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ችግር የግጭት ኣፈታት መከላከልን ኣስመልክቶ የምሁራን ሚና በሚል ያዘጋጁት ይህ ውይይት በሙሉ ምሁራን ተብለው የሚሳተፉት የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው ጉዳዩን የሕወሓት ስልጣን ለማስረዘም የተዘጋጀ እንደሆነ ተጠቁሟል፥ ራሳቸው በፈጠሩት የጎሳ ፖለቲካ ችግር ራሳቸውን እንደ ኣወያይ እና ችግር ፈቺ ኣድርገው መድረክ ላይ በመውጣት ሕዝቡን ለማዘናጋት የሚወጥኑት ሴራ መሆኑ ታውቋል።
በዚህ የፓናል ውይይት ላይ ራስ መንገሻ ስዩም ፣ የወያኔው ጄነራል ጻድቃን ገ\ኪዳን ፣ የወያኔ ፌዴራል ሚኒስትሩ ሲሳይ መለስ ፣ኣይቶ ዮሃንስ ወልደገብሬል መድረኩን ተቆጣጥረው ሌላውን ለማሸማቀቅና የበላይነት ለመያዝ የሚፍጨረጨሩበትን የውይይት መድረክ የወያኔው ፕሮፌሰር ፍሰሃጺዮን መንግስተይ የሚመሩት ሲሆን ለሕዝብ ክፍት ይሆናል ቢባልም ኣደራሹን ቀድመው በሕወሓት ኣባላት ከሞሉት በኋላ ኢትዮጵያውያን እንዳይገቡ እንደሚደረግ ካሁኑ ታቅዷል፥የለውጥ ሃይሎች በፓናል ውይይቱ ላይ ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል። ታማኝ ያልሆኑ የፖለቲካ ድርጅት ኣመራሮች እና የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች እንዳይገኙ ለማድረግ ኣስፈላጊው ሁሉ የሚደረግ ሲሆን በኣከባቢው 250 ፖሊሶች የሚመደቡ ይሆናል ሲሉ ምንጫችን ተናግረዋል። #ምንሊክሳልሳዊ
