“ከሻእቢያ ጋር ለመዋጋት ነው” የሚል የሐሰት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ወደ ጎንደር ተልከው የተገደሉ የፌዴራል ፖሊሶች ፎቶዎች
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
እነዚሁ ሰሞኑን በጎንደር የተገደሉ የፌዴራል ፖሊሶች ናቸው።
ወደ ጎንደር ሲሰማሩ አብዛኞቹ ከሻእቢያ ጋር ለመዋጋት ነው ተብለው ነው የመጡት። እዉነቱ፣ ሚሽናቸው ሳይነገራቸው። ተዋሽተው። በቦታው ሲደርሱ ግን አድርጉ የተባሉት ሕዝባቸው ላይ እንዲተኩሱ ነው። ያሳዝናል። ይሄ ሁሉ መሆን አለነበረበትም። ወደዚህ ደረጃ መደረስ አለነበረብት። ህወሃቶች እንጥፍጣፊ የሰላምና የ እርቅ መንፈስ ቢኖራቸው፣ ትንሽ እንኳን ከጥጋባቸው በረድ ቢሉ፣ ያሉ ችግሮችን በሰላም፣ በዉይይት መፍታት ይቻል ነበር።ግን ሰዎቹ አጋንንት የሰፈረባቸው ጥቅማቸውንና ስልጣናቸው ይጠበቅ እንጂ ለማንም ደንታ የሌላቸው ጭራቆች በመሆናቸው አገር ትታመሳለች።እነርሱ ለጆቻቸው ጋር እረፍት ዱባይና ፓሪስ ይሄዳሉ፤ የነዚህ ፖሊሶች ልጆች ግን ከዚህ በኋላ ያለ አባት ያድጋሉ። ያሳዝናል። ልብን ያደማል።