ማብራሪያ ስለ ኣዲሱ ፓርቲ Tekle Bekele


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ኣዲስ ኣድማስ ጋዜጣ በትናንት እትሟ የዜና ኣምዷላይ የቀድሞዉ የኣንድነት ፓርቲ ኣመራሮች ኣዲስ ፓርቲ መሰረቱ ብላ በመዘገቧ ቅርብም ሩቅም ያሉ ጓዶችና ደጋፊዎች በዉስጥ የመልእክት ሳጥን ኣላችሁበት ወይ የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡልኝ ይህችን ለመከተብ ተነሳሁ፡፡
የስልጣን ሃይሎች በባህሪ ይመሳሰላሉና ህወሓት ፓርቲዉን ለማፍረስ ከዉጪ የሚሰራዉን ያህል እነዚህ ኃላ ቀሮችም ከዉስጥ ሆነዉ የለዉጥ ሃይሉን ይጎትቱት ነበር፡፡ትግሉ እዉስጥም በመሆኑ የሚባክነዉ ጉልበትና እዉቀት ቀላል ኣልነበረም፡፡ሆኖም የለዉጥሃይሉ በክብር ተገቢ ቦታቸዉን በመስጠት ቢያሸንፋቸዉም ለዉጡን ያልፈለገዉ ህወሓት በምርጫ ቦርዱ ኣማካኝነት ፓርቲዉን ማፍረሱ ኣይዘነጋም፡፡ፓርቲዉ ከፈረሰ ማግስት ጀምሮ ያለፈዉን ሳይገመግሙና ከመጪዉ ሁኔታ ጋር ሳያገናዝቡ ወደ ፓርቲ ምስረታ በመግባት በሁለት ኣመታቸዉ ነፃነት የሚባል ፓርቲ መስርተናል ይላሉ፡፡እንኳን ደስ ያላቸዉ እላለሁ፡፡ እኔ በግሌ በኢትየጵያዊነት ጥላ ስር እስከተሰባሰበ ድረስ ከማንም ተቃዋሚ ፓርቲ ፊት ቆሜ እንቅፋት መሆን ኣልፈልግም፡፡ማታለልን፤ማደናገርንና ማጭበርበርን ግን ኣልደግፍም፡፡ጋዚጣዉ ኣንድ ሁለት ብሉ ለማይጠቅሰዉ ነገር ይህን ርእስ መጠቀሙ የነገር ነዉ ያስብላል፡፡ፕሬዝደንቱን ጨምሮ ከ13 የካብኔ ኣባላትና ምክትሎች ዉስጥ በዚህ ኣዲስ ፓርቲ ኣሁን ኣንድ የካብኔ ኣባልና ሁለት ምክትሎች ብቻ ናቸዉ ያሉበት፡፡ታድያ ጋዜጣዉ ተሳስቷል፡፡ጥቂት ወይም ኣብዛኛዉ ወዘተ የሚሉ ገላጭ ቃላትን መጠቀም ይችል ነበር፡፡የተሻለ መረጃም ለጋዜጣዉ ማሻሻጫ ይጠቀምባቸዉ ከነበሩት የቀድሞዉየኣንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኣባላት ያገኝ ነበር፡፡
ማብራሪያ
የቀድሞዉ ኣንድነት ኣብዛኛዉ ኣባለት ኣሁን የሚገኙት እስርቤት ታጉረዉ ነዉ፡፡ኣብዛኛዉ ኣንድነት ኣባላት የሚገኙት በስደት ነዉ፡፡ኣብዛኘዉ የአንድነት ኣባላት የሚገኙት ሜዳ ለይ ተበትነዉ ህዝቡ ዉስጥ ገብተዉ ትግል በማድረግ ነዉ፡፡ሰማያዊም ዉስጥ ገብተዉ እየታገሉ ያሉ በርካቶች ናቸዉ፡፡
በኣቶ በላይ ካብኔ ከኣቶ ብሩ ብርመጂና ኣቶ ደምሴ መንግስቱ በስተቀር ሌሎች በዚህ ኣዲሰ ፓርቲ ዉስጥ የሉበትም፤እነዚህን ሁለት ሰዎች ካብኔዉ ዉስጥ መካተት በወቅቱ የተቃወምኩት ቢሆንም ለማቻቻል በሚል ሆደ ሰፊነት ኣቶ በላይ ደንቡ በሚፈቅድለት መሰረት በልዩነት ኣካቶ ይዞኣቸዉ እንደመጣ ይታወቅ፡፡በወቅቱ ለኔ ከነዚህ ሰዎች ይልቅ ትግስቱ ኣወሉ ይሻለኝ ነበር!!
በዚህ ፓርቲ ዉስጥ ከተለመደዉ ኣካሄድና ባህል ባይላቀቁም ለኣቶ ተመስገን ዘዉዴና ለኣቶ ሽመልስ ሃብቴ ለእምነታቸዉ ጽናት የተለየ ክብር ኣለኝ፡፡እነሱም ቢሆኑ ግን የስልጣን ሃይሎች ባህሪ የተለበሱ ናቸዉ፡፡ለለዉጥ ይለግማሉ!!
ኣሁን ባለን ልምድ ፓርቲ ከተመሰረተ ከነበረዉ ላይ ኣዲሰ ነገር ጨምሮ (በፕሮግራም፤በድርጅታዊ ባህል፤በሰዉ ሃይል፤መሰርትና ስትራተጂ…) የሁሉም ቤት ሊሆን በሚችልበት ሁኔታ እንጂ ከነበረዉ ላይ ጨልፎ የስም ወራሽነትን ለማሳየት ብቻ መሆን የለትም፡፡በሰላማዊ ትግሉ ፅኑ እምነት ካለ ፓርቲ ማቆም ለዚህ ትዉልድ የሁለት ቀናት ሰራ ነዉ፡፡እነማን ምን መሆናቸዉን ካለፉት ጉዞኣችን በቂ ልምድ ወስደናል ብየ ኣስባለሁ፡፡ፓርቲ ለመመስረት ማስቀረት ይገባቸዉ የነበሩ በህይወት ያሉ ፓርቲዎች በተለያዩ ምክንያቶች ሃላፊነታቸዉን በሚገባ ኣልተወጡምና ሰፊ መሰረት ያለዉ ፓርቲ መስርቶ ህዝባዊ ትግሉን መቀላቀል የወቅቱ ጥያቄ ነዉ ብየም ኣምናለሁ፡፡