አስመራ ያለው ሰውየ ጥዋት ከነጅሎ ጋር ቁርስ በልቶ ምሳ ሳአት ላይ አራት ኪሎ ካለው ወንድሙ ጋር በስልክ እያወራ ይስቅባቸዋል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አስመራ ያለው ሰውየ ጥዋት ከነጅሎ ጋር ቁርስ በልቶ ምሳ ሳአት ላይ አራት ኪሎ ካለው ወንድሙ ጋር በስልክ እያወራ ይስቅባቸዋል

የጨነቀው እርጉዝ ያገባል!!! (ናትናኤል ኣስመላሽ)

ከእንቅልፋቸው ሲነቁ አራት ኪሎ ሁሌም የሚታያቸው እን እንትና ሲጨንቃጨው እርጉዝ አገቡና፣ የእርግዝናው ጊዘ ከዘጠኝ ወር ወደ ዘጠና ወር ተራዘመባቸው ፣አሁንም ቢሆን ተስፋ ሳይቆርጡ ይጠብቃሉ።እስካሁን ድረስ ከእርጉዝዋ ሚስታቸው ልጅ መጠበቅ የሰለቻቸው ብዙዎቹ ናቸው፣ እነ እንትና ግን ኣልገባ አላቸው። እነ እንትና ከኣስመራ አራት ኪሎ ለመግባት፣ አሁን አስመራ ላይ ሆነው አራት ኪሎ ጋር ካለው ወንድሙ ጋር ለመዋጋት ያስባሉ። ኣስመራ ያለው ሰውየ ሁሌ ይስቅባቸዋል። በጥርሱ እየሸኘ እነዚህ እብዶች ብቻ ሳይሆኑ ጅሎችም ጭምር ናቸው ይላል።

አስመራ ያለው ሰውየ ጥዋት ከነጅሎ ጋር ቁርስ በልቶ ምሳ ሳአት ላይ አራት ኪሎ ካለው ወንድሙ ጋር በስልክ እያወራ ይስቅባቸዋል፣ ሚስጥራቸው ሁሉ ከ ሀ እስከ ፐ ይናገራል። ማን የት እንዳለ የት እንደዋለ፣ምን እንዳለ ይናገራል። ማን በማን ፓስፖርት ፣በምን ስም እንደሚንቀሳቀስ ይናገራል። ማን በ የትኛው የአውሮፕላን ማረፍያ በስንት ሰአት እንደሚገባ ይናገራል። ይህ ሁሉ ሚስጥር ለብዙ አመታት ያጠና የአራትኪሎው ሰውየ፣ በፈለገውን ቀን እና ሰአት የፈለገውን ተላላኪ፣ባንዳ፣እቁብ ሰብሳቢ አፍኖ ካሻው ቦታ ያስራል። እነ እንትና አሁንም የድሮ ፍቅረኛሞች ኣጣልታቹ ጎጆ ለመውጣት ካሰባቹ ኣይሳካላቹም። እነሱ በናንተ ዶላር ይጠጣሉ ይበላሉ። እናንተ ደግሞ ፒቲሽን ትሞላላቹ። ድሮስ ግም ለግም ተያይዛቹ መች ቁምነገር ትሰራላቹ።

Natnael Asmelash's photo.