የምዕራብ ትግራይ-ኤርትራ-ሱዳኑ አደገኛና ውስብስብ መረብ ከ60 በላይ ሕይወት በላ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የምዕራብ ትግራይ-ኤርትራ-ሱዳኑ አደገኛና ውስብስብ መረብ ከ60 በላይ ሕይወት በላ፤ ያሳዝናል!

በኢትዮያ- ኤርትራ- ሱዳን የተዘረጋውና ከፍተኛ የኤርትራ ወታደራዊ መኮንኖች፣ በትግራይ የምዕራባዊ ዞን ሓለፊዎችና የፖሊስ መኮንኖች፣ በርካታ የሱዳን ባለስልጣናት ወ.ዘ.ተ ተዋናይ የሆኑበት እጅግ ውስብስብ የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር መረብ ባለፉት ጊዜያቶች ያለአንዳች ከልካይ ከትግራይ ምዕራባዊ ዞን (በተለይም ከማይካድራ፣ አደባይ፣ ሑመራ ወ.ዘ.ተ) በርካታ ህጻናትን አታሎም አስፈራርቶም ወደ ሱዳን በመውሰድና በማገት 40 ሺህ ብር መክፈል የቻሉትን እያሳለፈ፣ መክፈል ያልቻሉትን ደግሞ ለበደዊኖች በመሸጥ ኩላሊትና ሌሎች የውስጥ ዕቃዎቻቸውን ተዘርግፈው እንዲሸጡ ሲያደርግ የነበረና ለብዙ ሕይወቶች መጥፋት ተጠያቂ የሆነ እጅግ ውስብስብ፣ ከልካይ የሌለው አደገኛ መረብ ነው፡፡

ዛሬ እንደተሰማው ይህ እጅግ የተጠላለፈ መረብ የUN መኪና ለማስመሰል ነጭ ሻራ አስለብሶ፣ UN የሚል ፅሑፍ ፅፎባት፣ 70 ወጣቶች አጭቆባት በፍጥነት እየከነፈ ድንገት ባጋጠመ የመገልበጥ አደጋ ከመተማ-ገዳሪፍ ባለው መስመር 70 ኤርትራውያን ጭና ስትጓዝ ለ62 ሰዎች ወዲያወኑ መሞታቸውንና ቀሪዎቹ ላይ ደግሞ ከፍተኛ አደጋ መድረሱን ታውቋል፡፡