የሻእቢያና ወያኔ ጦርነት መነሻ የከዱ የሳዋ ሰልጣኝ ወጣቶች ድንበር ሲያቋርጡ ተኩስ ተከፍቶባቸው መያዛቸው ነው።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የሻእቢያና ወያኔ ጦርነት መነሻ የከዱ የሳዋ ሰልጣኝ ወጣቶች ድንበር ሲያቋርጡ ተኩስ ተከፍቶባቸው መያዛቸው ነው። ወያኔ ደንብሮ ለተኩሱ ምላሽ ሰጥቷል

በሻእቢያ እና ወያኔ መካከል ውጊያ የተቀሰቀሰው ከሰራዊት ያመለጡትን ኣባላቱን ለመያዝ የኤርትራ መንግስት በከፈተው ተኩስ የወያኔ ሰራዊት በኣጸፋው በተኮሰው ጥይት መሆኑ ምንጮች ኣረጋግጠዋል፥የወያኔ ሰራዊት የሻእቢያን ጥቃት ለመከላከል መልሶ መተኮሱ ተረጋግጧል፥ ወያኔ በከፍተና ደረጃ ተሸብሮ እንደነበር ምንጮቹ ኣረጋግጠዋል፥ ወታደሮች ከድተው ለሻእቢያ እጃቸውን ይሰጡብኛል የሚል ፍራቻ እንደነበረው ምንጮቹ ጨምረው ተናግረዋል።

በኣከባቢው ሰፍረዋል የተባሉ የሻእቢያ ተቃዋሚ ጥምረት ታጣቂዎች በፍጹም እንዳይንቀሳቀሱ መደረጉ ተሰምቷል፥ቅዳሚ እኩለ ለሊት ላይ የኢትዮጵያን ድንበር ኣቋርጠው ለመግባት የሞከሩ የሳዋ ሰልጣኞች ድንበሩን ለማቋረጥ ጥቂት ሲቀራቸው የሻእቢያ ሰራዊት ኣባላት ተኩስ ከፍተው ወጣቶቹን በቁጥጥር ስር ካዋሉ በኋላ በጾረና ግንባር የሚገኘው የወያኔ ሰራዊት በቀጥታ ከሻእቢያ ሰራዊት ጋር ውጊያ መግጠሙ ሲታወቅ ተይዘው የተመለሱትን የሳዋ ሰልጣኝ ወጣቶች ግን ለማስመለስ ባለመቻሉ ውጊያው ቆሟል፤በዛላምበሳ ይኑሩ ኣይኑሩ ማረጋገጫ ያልተገኘላቸው የሻእቢያ ተቃዋሚ ድርጅቶች ወታደሮቻቸው ግጭቱን በተመለከተ እስካሁን የሰጡት ኣስተያየት የለም። Click Source Minilik Salsawi

Image