የደሕንነት ቢሮው ስብሰባና የመኮንኖች ጉርምርምታ … ዝም ያለ ሁሉ ሞኝ ኣይደለም:: ‪


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የደሕንነት ቢሮው ስብሰባና የመኮንኖች ጉርምርምታ … ዝም ያለ ሁሉ ሞኝ ኣይደለም::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Eritrea‬ ‪#‎Zalambesa‬ ‪#‎TsoronaFront‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የደህንነት ተቋሙም ይሁን ወታደራዊው እዝ ማንኛውም ጦርነት ቢደረግ ሕዝብ ከጎኑ አንደማይቆም በስብሰባ ኣረጋግጦታል፤ የሕወሓት የደህንነት ባለስልጣናት እና ወታደራዊ ኣዛዦች ስብሰባ ተቀምጠው በጉዳዩ ዙሪያ የተለዋወጡት ሃሳብ አንዱ ለኣንዱ ስላልተዋጠለት በከፍተኛ ንትርክ ስብሰባቸውን ሳይቋጩ በይደር ኣቆይተውታል፤ ጦርነቱ የሃስት ነው ታማኝነት የለውም።ስህተት ነው ከሚሉት ጀምሮ የኣከባቢውን ወታደራዊ ትኩሳት ለመለካት የተደረገ ነው ጦርነቱ ኣስፈላጊ ኣይደለም መተነኳኮሱ ለምን ኣስፈለገ የሚሉ ሃሳቦችና ጥያቄዎች እስከ ጦርነቱ ከተጀመረ ለምን ማቆም ኣስፈለገ ዝም ያለ ሁሉ ሞኝ ኣይደለም:: በቀጣይነት ሻእቢያን ለመደምሰስ መቀጠል ኣለበት የሚሉ የዋሃን መኮንኖችን የታዩበት ስብሰባ ነበር፤ ከዚህ ቀደም በጦርነቱ ጉዳይ በረከት ስምዖን ያለውንም ኣስተያየት ኣንስተው ከኤርትራ ጋር የሚደረግ ጦርነት የኢሕኣዴግን መንግስት መቃብር ማፋጠን ነው እስከሚል ኣስተያየት ተሰምቷል፥ ስብሰባው በይደር የተላለፈ ሲሆ የሕወሓት ከፍተኛ ኣመራሮች ይዘውት የሚመጡት ማጠቃለያ ሃሳብ አየተጠበቀ ነው።..//…

የጦርነት ወሬ ሕዝቡን ኣንገሽግሾታል።ለእናት ኣገር መሞትን የሚጠላ ማንም የለም።በደርግ ስርዓት በኣንድነት ሽፋን ከፈቃደኛ ዘማቾች ጀምሮ እስከ ታፍሰው የዘመቱ ከብሄራዊ ውትድርና ጀምሮ አስከ ለብለብ ሰልጣኝ ተማሪዎች ወታደራዊ ኣምባገነኖችን በስልጣን ለማቆየት በተደረገ ጦርነት ሲሰዉ የደርግ መኮንኖች ለ ኤምፔሪያሊስት ሃይሎች አና ቅጥረኞቻቸው ወያኔና ሻእቢያ ኣገሪቷን ኣሳልፈው ሸጠው ወታደሩን ሜዳ ላይ ለማኝ ኣድርገውታል፤ቀጣዩም የወያኔ ኣምባገነን የወንበዴዎች ቡድን በባድመ ምክንያት ባደረገው ጦርነት ከ፹ ሺህ በላይ የሚልቁ ዜጎች ደመ ከልብ በማድረግ ኣላማውን ዘንግቶ ውነቱን በመካድ ወጣቱን ደመ ከልብ ኣድርጎታል፤በዚህ ደግሞ ሕዝቡ ትልቅ ቂም ቋጥሯል ስለዚህ ይህን ሕዝብ ጦርነት ኣለብኝ ና ዝመት ከሚባል መሃል ኣገር የተሰቀለውን ኣገዛዝ ቢያወርድ ይቀለዋል።

ሕዝቡ ካለፉት ኣገዛዞች ይሁን ኣሁን ካለው ዘረኛ ኣገዛዝ ብዙ ተምሯል፥ዝም ያለ ሁሉ ሞኝ ኣይደለም፤ ጊዜና ወቅት ይጠብቃል።መሃል ኣገር ላይ ተዘፍዝፎ ሃገርና ሕዝብን አያሰቃየ ለሚኖር ኣገዛዝ መዝመት ሳይሆን መሳሪያውን ወደ ኣገዛዙ ማዞር ጽድቅ ነው፥የወያኔ ኣገዛዝ በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ ኤርትራ ላይ ያወጣውን ዘገባ ተከትሎ ሲያራግብ የነበረ ሲሆን ጉዳዩን ኣመድ በዱቄት ይስቃል ኣድርጎታል፥የሚሉሽን ባልሰማሽ እንደተባለው የራሱን ጉድ ምን እንደሚባል እያወቀ እና እየሰማ ባልሰማ ሙድ የራሱን እያሳረረ የሌላውን ሲያማስል ሰሚ ጆሮ ሊያገኝ ባለመቻሉ ኣትኩሮት በማስፈለጉ የድንበር ላይ ጦርነት ገጥሟል፥ችግሮቻችንን የምንፈታው መሃል አገር ላይ የተሰቀለውን ኣገዛዝ በማውረድ እንጂ ከጎረቤቶች በመዋጋት ኣይደለም።ጦርነትን ኣስመልክቶ ከኣምባገነኖች ጎን መቆም የሕዝብን ስቃይ በማበርታት የጨቋኞችን እድሜ ማስረዘም ነው። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬