የኢንተርኔት ጽሑፎችን ለመቆጣጠር ህግ ሊወጣ ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Addis Admass – በኢንተርኔት የሚሰራጩ ጽሑፎችን፣ ምስሎችን፣ ቪዲዮዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለመቆጣጠር፣ መንግስት አዲስ ህግ እያዘጋጀ ነው፡፡
ህጉ የሚዘጋጀው በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሲሆን፤ በኢንተርኔት የሚሰራጩ መረጃዎችንና በኢንተርኔት የሚከናወኑ ስራዎችን በሙሉ የመቆጣጠር ስልጣን እንዳለው ሚኒስቴር መ/ቤቱ ገልጿል፡፡ የኢንተርኔት መረጃዎችን ለመቆጣጠር የህግ ሰነድ ለማዘጋጀትም፣ ከሁለት ኩባንያዎች ጋር ጥናት ለማካሄድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውል ተፈራርሟል፡፡
“Grail Consulting and Project Management Services” የተባለ የውጭ አገር ኩባንያ ጥናቱን ሲያካሂድና፤ “Perago Information Systems” የተባለ የሀገር ውስጥ ኩባንያ በአጋርነት ይሰራል ብሏል፡፡ የመንግስት አካላት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማነጋገርና መረጃ በመሰብሰብ ጥናቱ ይካሄዳል ብሏል – ሚኒስትሩ፡፡
የኢንተርኔት የመረጃ ጠለፋንና ተመሳሳይ ድርጊቶችን፤ እንዲሁም የመንግስት መርማሪዎች ስልጣንን በሚመለከት በቅርቡ አዲስ ህግ ተዘጋጅቶ የወጣ ሲሆን፤ በኢንተርኔት የሚሰራጩ መረጃዎችን ላይ የሚደረጉ ቁጥጥሮችንም ያካተተ እንደነበር ይታወቃል፡፡