በ10 ሺ የሚቆጠሩ ቤቶች ይወድማሉ !!! የትግራይ መንግስት የደረሰበት የኣስተሳሰብ ዝቅጠት እጅጉን ኣሳሳቢ ነው።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


እውነት ይህ የጉንበት 20 ፍሬ ሳይሆን የጉንበት 20 እሬት( ናይ ጉንበት 20 ፍረ ተለይ ኾነስ ዕረ) ነው።

የህወሓት መንግስት ሕገ ወጥ ግንባታ በሚል ሰበብ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ የድሃ ኑዋሪ ቤቶች ወደ ኣፈር እየቀየራቸው ይገኛል።

የዚህ ወደር የማይገኝለት ግፍ በማይካድራ 700 ቤቶች ከነ እቃቸው በማውደም የጀመሩ ፋሺሽታዊ ምግባር ነው።
የማይካድራ ህዝብ ግፉ ለመከላከል ያደረገው ጥረት ከቁጥሩ በላይ ልዩ ሃይል ኣሰልፎ ኣውድሞታል።
ይህ ተግባር በትላልቅና በገጠር ከተሞች በስፋትና በዘመቻ መልክ እየተካሄደ ይገኛል።
ለምሳሌ በሰሓርቲ ሳምረ ወረዳ ግጀት ከተማ የሚገኙ ከ45 ዓመት በፊት የተሰሩ ቤቶች ጭምር ሕገ ወጥ ተብለው እየፈረሱ ይገኛሉ።

ኣንድ ምሊሻ የግጀት ኑዋሪ የግፉ ሰለባ ከሆኑ ኣንዱ ነው። የከተማዋ ሓላፊዎች ቤቱ እያየ ማፍረስ ፈርተው ስብሰባ ስላለን እንሂድ ብለው ይወስዱታል። ባልጠበቀው መንገድ ጠብመንጃው ቀሙትና ወደ ቤቱ መለሱት። ሰውየው በዓይኑ ያየው ለማመን ተቸገረ። እቃው እንኳን ከቤቱ ኣላስወጣም። ያው ቤቱ ከነንብረቱ ኣወደሙት። ሰውየው ከ1973 ዓ/ም ጀምሮ የህወሓት ሽግ ወያነ(ምልሻ) ሆኖ ያገለገለና የታገለ ነበር።
ህወሓት ማለት ውለታቢስ ድእጅት ነው። ይኸው ታግሎ ለስልጣን ያበቃው ኣንድ ድሃ ገበሬ ቤቱና ንብረቱ በማውደም የድሃ ድሃ ኣደረጉት።
ከመቶ በላይ ቤቶች የግጀት ከተማ ቤትች ይፈርሳሉ። ባለቤቶቹ ተመልሰው በሊዝ ተጫርተው እንዲገዙ ይገደዳሉ።
ቤታቸው የፈረሳቸው የግጀት ኑዋሪዎች ኣብየቱታ ከቀበሌ እስከ ክልል ኣቅርበው ሰሚ ኣላገኙም። በመጨረሻ ኣብየቱታ ለማቅረብ ትናንት ሓሙስ 18 /09/08 ወደ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን መቐለ ቅርንጫፍ(የህወሓት ፅህፈት ቤት ፊት ለፊት የሚገኘው) ሂደው ችግራቸው ኣቅርበው ኮሚሽኑ ኣንድ መፍትሄ እንዲያበጅላቸው ጠየቁ።
ከኮሚሽኑ ሃላፊዎች የጠበቃቸው መልስ “መንግስት ሕገ ወጥ ቤቶች የማፍረስ ሰፊ ዘመቻ ጀምረዋል። ይሄ ደግሞ ልንደግፈው እንጂ ልንቃወመው ኣይገባም። እናንተም በሰላም ብትቀበሉት ይሻላል። የሚል መልስ ሰጥተው መለሷቸው።
የግጀት ኑዋሪዎች ይሄ መልስ ከሰሙ በኋላ ወደ እምባ ጠባቂ ተቋም ሊሄዱ የያዙት እቅድ ሰርዘው ተሰብስበው ኣልቅሰው ወደ ፍርስራሽ ቤታቸው ተመለሱ።
የማውደም እቅዱ ከተያዘላቸው ህዝቦች መካከል የእንደርታ ህዝብ ሌላኛው ባለ ክፉ ዕጣ ነው።
የኣይናለም ከተማ ቤቶች እንዲፈርሱ በእቅድ ከተያዙት ቤቶች ከጃንሆይ ግዜ እስከ ኣስራ ኣምስት ዓመት በፊት የተገነቡ ቤቶች ናቸው።

የዓይናለምና ሌሎች የመቐለ ኣዋሳኝ ቀበሌዎች ቤቶች እንዲፈርሱ ለሰኞ እቅድ ተይዘዋል።

የህወሓት መንግስት ልክ በካንሰር ህመም እንደተያዘ ህመምተኛ የሚሞትበት ቀን የሚታወቀውና እጅጉን ተስፋ ቆርጠው ቀንዋን የሚጠብቀው ህዝባችንም ከሞቀችው ደሳሳ ጎጀው ወጥቶ ወደ ጎዳና የሚዳረጉባት ቀን ተስፋ በመቁረጥ እየተጠባበቀ ይገኛል።

ዘመቻው በመላ ትግራይ የሚገኙ ትላልቅና ኣነስተኛ ከተሞች የሚገኙ በ10 ሺ የሚቆጠሩ ቤቶች ይወድማሉ።
በዛው ልክ በመቶ ሺ የሚቆጠር ህዝብ ቤት ኣልባ በመሆን ለጎዳና ተዳዳሪነት ይጋለጣል።

ህወሓት ለትግርይ ህዝብ ክፉ ወይም ደመኛ ጠላት ሁኖበት ይገኛል። ክረምት በቀረበበት ግዜ ጠብቆ መጠልያ ኣልባ ማድረግ ከደመኛ ጠላት የማጠበቅ እንጂ የትኛው ወዳጅ ያደርገዋል ???

በህግ ማስከበር ሽፋን ህዝብ ቤት ኣልባ ኣድርጎ የድሃድሃ ኣድርጎ የመግዛት የህወሓት እቅድ እቃወማለው።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

it is so.

Amdom Geberslassie