ማንም ከማንም በላይ አይደለም::የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሁሉ የፌዴራሉ ቋንቋ ቢሆኑ ማንም የሚጠላ የለም:
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ማንም ከማንም በላይ አይደለም::የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሁሉ የፌዴራሉ ቋንቋ ቢሆኑ ማንም የሚጠላ የለም:: #Ethiopia #FederalLanguages #Ethiopianism #Equality #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi – Ethiopian DJ ኢትዮጵያዊነት ማለት ፍቅር ነው:;ኢትዮጵያዊነት ማለት አንድነት ነው::ኢትዮጵያዊነት ማለት የማይላቀቅ ክቡር መንፈስ ነው::ብዙ ማለት ይቻላል ስለ ኢትዮጵያዊነት… ኢትዮጵያውያን እኩል መብት እኩል ሃገር እኩል ተጠቃሚነት ሊኖራቸው ይገባል::ማንም ከማንም አያንስም::ማንም ይሁን ማንም በአንድነት ስም ሊጫን የሚፈለግ ግዞት አሊያም በአንድነት ስም ሕዝቦችን ቅኝ ለመግዛት የሚፈለግ ከሆነ አደጋው የከፋ ነው::በአንድነት ስም ተደብቆ የጎሳ ፖለቲካን ለማጦዝ አሊያም የሌላውን ኢትዮጵያዊ ጥቅም ቀብሮ የአንድን ብሄር ብቻ ለማራገብ መሞከር ይህም ውሎ ይደር እንጂ የከፋ አደጋ አለ::ኢትዮጵያዊነት በዘመነ-ወያኔ አመጣሹ የጎሳ ፖለቲካ እና የጎሳ ፌዴራሊዝም በቂም ለማኖር የሚጥሩ ያልበሰሉ ፖለቲከኞች በጥላቻ ለመሙላት ቢጣደፉም አልተሳካላቸውም::
ኢትዮጵያ እጅግ በርካታ ብሄረሰቦች እና ቈቋዎች በስፋት የሚነገሩበት ውብ ሃገር ናት::በፍቅር እና በአንድነት በመከባበር እና በመተሳሰብ የኖረን ሕዝብ በጎሳ ፌዴራሊስም ተብትቦ ለመበታተን ባለፉት ሃያ አምስት አመታት ያልተቧጠጠ ጉድ የለም:: በአሕጉራችን የብቸኛ ፊደል ባለቤት የሆነውን አማርኛ እንደ ቅኝ ገዢዎች ቋንቋ አድርጎ ለማሳየት በመሞከር የቋንቋ ብጥብጥ ለመፍጠር የሚጥሉ ጭፍኖች ዛሬም ድረስ እየለፈለፉ ይገኛሉ::በሃገሪቱ የሚነገሩ እንደ አማርኛ ኦሮሚኛ ጉራጊኛ ሱማሊኛ ትግሪኛ እና የመሳሰሉት በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ቋንቋዎች በመላው ሃገሪቱ የመንግስት መጠቀሚያ ቢሆኑ በየትምህርት ቤቱም ቢሰጡ ማንም የሚተላ የለም::እንኳን ኢትዮጵያዊ ቋንቋዎችን ይቅርና ተነጮችን ቋንቋ ከፍለን እንማር የለም እንዴ ?
ጥቂቶች በዘረኝነት የተጀቦኑ ግለሰቦች የብሄራቸውን ቋንቋ ብቻ አተልቀው የልላውን ለመደፍጠጥ የሚያደርጉት ሙከራ በፍጹም አይሳካም::በየማህበራዊ ድህረገጹ መጻፍ እና መሬት ላይ አውርጄ እተገብራለሁ ማለት የተለያየ እና የማይገንኝ ሲሆን መልሱም በባዶ ውጤት መመለስ ነው::በመጀመሪያ የሕዝቦችን እኩልነት ልንቀበል ይገባል::በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብሄሮች ባህል ቋንቋ እና ተውፊት ሁሉ የራሳችን አድርገን ልንቀበል ይገባል::የሌላውን ሳናከብር የኛ የሚያከብርልን የለም:: ተጽእኖ ፈጥረን መላ እናመጣለን ብሎ ማሰብ አደጋው የሚተርፈው ለራሱ ለሚንቀዥቀዠው አካል ነው::አሁንም የምለው ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ነው::ማንም ከማንም በላይ አይደለም:: የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሁሉ የፌዴራሉ ቋንቋ ቢሆኑ ማንም የሚጠላ የለም::#ምንሊክሳልሳዊ
