በማይካድራ በመንግስት ሃይሎችና በህዝቡ መሃከል ከፍተኛ ግጭት ተቀሰቀሰ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በማይካድራ በመንግስት ሃይሎችና በህዝቡ መሃከል ከፍተኛ ግጭት ተቀሰቀሰ።

‪#‎Maykadra_Tigray_Ethiopia_Protest‬.

“… ቤታችን ከሚፈርስ ኢህኣዴግ ይፍረስ …”
የማይካድራ ህዝብ

በማይካድራ ከተማ “የቤቶች ኣፍራሽ ግብረ ሃይል” ( የትግራይ ልዩ ሃይል፣ ፖሊስ፣ ምልሻ፣ የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ከንቲባ የሚመሩት) ሃይልና በከተማዋ ህዝብ መካከል ከፍተኛ ግጭት ተነስነስተዋል።

የህዝቡ ቁጣ የተቀሰቀሰው በማይካድራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የተቋቋመው የቤቶች ኣፍራሽ ግብረ ሃይል ድንገት ተነስቶ በከተማዋ ቀጠና 5 የሚገኘው የወይዘሮ የሺ በርሀ፣ ባሳዝነው ቸኮል፣ ሃፍተ ወርቅነህ፣ ዘርኣይ በርሀ የተባሉ 4 ቤተ ሰቦች ኣቤቱታ ለማቅረብ ከነ ልጆቻቸው ሑመራ በሄዱበት ወቅት ቤቶቹ ከነ ሙሉ እቃው ኣፍርሰው ሙሉ ንብረታቸው እንዲወድም በማድረጋቸውና ዝናብ ዘንቦ ሙሉ እቃቸው ከጥቅም ውጭ እንዲሆን በማድረጋቸው ነው። ህዝቡ የዚህ ግፍ ሰለባ የሆኑት ቤተሰቦች በቅፅበት ለጎዳና ተዳዳሪነት መጋለጣቸው የተመለከተው የከተማዋ ህዝብ ከፍተኛ ቁጣና ተቃውሞ በኣፍራሽ ግብረሃይሉ እንዲያስነሳ ምክንያት ሆኖበታል።

ይህ ክስተት ሰኞ 08/ 09/08 ዓ/ም ያጋጠመ ሲሆን የህዝብ ቁጣ ወደ ግጭት ያደገው ደግሞ ትናንት ማክሰኞ 09/ 09/ 08 ኣፍራሽ ግብረ ሃይሉ ዳግም ሃይሉ ኣጠናክሮ 198 ቤቶች ለማፍረስ ስራው ኣንድ ብሎ ሲጀምር ነው።

ማዛገጃ ቤቱ “ህግ ወጥ ግንባታ ናቸው” ብሎ መፍረስ ኣለባቸው ያላቸው 700 ቤቶች ነበሩ።

በመሃሉ የከተማዋ መሃንዲስና ከንቲባዋ በመመሳጠር ኑዋሪዎች ሙስና እንዲከፍሉና ህጋዊ የባለ ቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ተዘጋጅቶ እንዲሰጣቸው እንደሚደረግ ለያንዳንዱ ባለቤት በደላሎች ተነግሯቸዋል።
ለመክፈል ፍቃደኞች የሆኑ ባለ ቤቶች ህጋዊ ተደረገላቸው። ለመክፈል ፍቃደኛ ያልሆኑ 198 ቤቶች እንዲፈርሱ ተወሰነ። የውሳኔው ትግበራም በከተማዋ ከንቲባ መሪነት በወዘሮ የሺ በርሀ ኣንድ ብሎ ጀመረ፣ ሌሎች 3 ቤቶችም ከነሙሉ እቃቸው ወደሙ። የግፉ ሰለቦች ንብረታቸው እንኳ እንዲያስወጡ እድል ሳይሰጡ ቤታቸው ኣመድ ኣደረጉት።

የከተማዋ መሃንዲስ የነበረና ከሃላፊዎች በመመሳጠር ሙስና ተቀብሎ “ህጋዊ ሰነድ” የሸጠው ወጣት ከኣገር ኮብልሎ ኣውሮፓ ገብተዋል እየተባለ ነው።

ክፍያው ለመክፈል ፍቃደኛ ያልሆኑ ሰዎች ከ15 ቀን በፊት በኢንፎርማል መንገድ ቤታቸው እንደሚፈርስ በመስማታቸው ተሰባስበው ወደ ከንቲባው ኣብየቱታ ሊያሰሙ ሄዱ። “ቤቶቹ መፍረስ ኣለባቸው” የሚል ምላሽ ተሰጣቸው።

“በውሳኔህ ኣንስማማምና በፅሑፍ ኣድርግልን፣ የይግባኝ መብታችንም ይከበርልን?” ብለው ሲጠይቁ “ማህተም የለም” በማለት የሰሩት ሙስና እንዳይጋለጥ በመፍራት ተሯሩጠው ወደ ማፍረስ ተግባር እንደገቡ ኑዋሪዎቹ ይናገራሉ።

ኑዋሪዎቹ ከ15 ዓመት በላይ የኖሩበትና በህጋዊ መንገድ የሰሩት ቤት እንደሆነ በመግለፅ ከበላይ ኣካላት እንዲገናኙ የይግባኝ መብታቸው እንዲፈቅድላቸው ጠየቁት።
ፍትህ እንዳያገኙ የይግባኝ መብታቸው በመንፈግ በሃላፊዎቹ ታፍነው እንዲቀሩ መገደዳቸው ይገልፃሉ።

ጠብመንጃ በታጠቁ ሃይሎችና ድንጋይና ዱላ በያዘው ህዝብ መካከል የተካሄደው ፍልሚያ ህዝቡ ታጣቂዎች ወደ መጡበት በማባረር ቤቶች እንዳይፈርሱ እንዲቆዩ ኣድርገዋል።

ኣፍራሽ ግብረ ሃይሉ ከሚያፈርሰው ሰፈር ተባርሮ ወደ ከንቲባው ፅህፈት ቤት ከተመለሰ በኋላ 4 ሰዎች የ198 ሰዎች ውክልና ኣስይዘው ወደ ማዘጋጃቤቱ በመላክ ከከንቲባው ለመወያየት ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቶ ቐሺ ጎይተኦም በርሀ ኻሕሳይ የኮሚቴው ኣስተባባሪ ተቀብሎ እንዲታሰሩ ኣድርገዋል።
የቐሺ ጎይተኦም መታሰር የህዝብ ቁጣ እንዲነሳሳና ግጭቱ እንዳዲስ እንዲያገረሽ ምክንያት ሆኖዋል።
ለቐሺ ጎይተኦም በርሀ ኻሕሳይ መታሰር የተሰጠው ምክንያ “የተቀዋሚ ድርጅቶች ተልእኮ ይዞ ተገኝተዋል” የሚል የፈጠራ ክስ ኣቅርበዋል። ልዩ ሃይሉ የቐሺ መታሰር የከንቲባው ትእዛዝ ብቻ መሆኑ ገልፀዋል።

ህዝቡ ኣፍራሽ ግብረ ሃይሉ ሲያባርር “…ቤታችን ከሚፈርስ ኢህኣደግ ይፍረስ…” የሚል መፎክር እያሰማ ነበር።

ማይካድራ ከተማ በዚ ሶስት ወራቶች ወጣቶችዋ ከትምህርትቤታቸውና ዩኒፎርማቸው ሳይቀይሩ፣ ከቤታቸውና ሰሃራ ሞቱ የተባሉ ጓደኞቻቸው የቀብር ዳስም ሳይቀር ተነስተው ወደ ሰሃራ የሚወሰዱበት የሚወሰዱበት፣ ወላጆች “ከ120 እስከ 140 ሺ ብር ላኩ ካልሆነ ልጆቻቹ ለኩላሊት ነጋዴዎች እይሸጣሉ” ራሳቸው የክልሉ ባለስልጣናትና ከፍተኛ ወተሃደራዊ ባለስልጣናት ድጋፍ ኣለብን በሚሉ ደላሎች እየተስፈራራ የሚገኝ፤ ገንዘብ ላልተላከላቸው 17 ወጣቶች ደግሞ “በውሃ ጥም ሞቱ” እየተባሉ መርዶ የሚሰማባት ኣሳዛኝ ከተማ ሁናለች።

የተለያዩ የትግራይ ወረዳዎች ኑዋሪ ህዝብ የህወሓት ኣገዛዝ የሚያደርስበት ግፍና ዓፈና መቋቋም በመሰላቸቱ የራሱ የሃይል ኣማራጭ እየተጠቀመ ይገኛል።

ከቅርብ ወራቶች ብቻ ብንነሳ የመቐለ ባለ ባጃጅ ወጣቶች፣ የእምባስነይቲ የወረዳችን የይመለስልን ጥያቄና የህወሓት ውክልና መንፈግ ወዘተ መጥቀስ ይቻላል።

“… ቤታችን ከሚፈርስ ኢህኣዴግ ይፍረስ …” የማይካድራ ህዝብ

#Maykadra_Tigray_Ethiopia_Protest.

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

it is so.

Amdom Gebreslasie's photo.
Amdom Gebreslasie's photo.
Amdom Gebreslasie's photo.

Amdom Gebreslasie's photo.