መናገር የሚጎዳውን ትግል ፥ ዝምታ አያድነውም ( ሄኖክ የሺጥላ )


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የጋራ ሀገር አለን ብሎ የሚያምን ሰው ፥ ለ ዲሞክራሲ ግንባታ እታገላለሁ ብሎ የሚያስብ አካል እና የዛ አካል ውላጅ ፥ ሃሳብን በነፃነት ስለመግለፅ በሚደሰኩርና የዜጎች መብት ይከበር ዘንድ ( እንዲከበር ) ነው የምታገለው የሚል ኣካል ፥ ትንንሽ ( ደቃቃ) ሃሳቦች ያስፈሩታል ብለን አንገምትም ። ስለ እኩልነት እያወራን እራሳችን እኩል መሆን ያቃተን ከሆንን ፥ የማንፈቅደውን ለመሆን የምንታገል ነን ማለት ነው !

ስለ ሃገራችን ያገባናል ያሉት ሰዎች የሚያደርጉት ትግል ሁሉ ያገባናል ። እንኳን ስለ ሃገራቸው ገዷቸው በርሃ የገቡት ፥ የምንግዴዎቹም አካሄድ ያገባናል ። ምንግዴዎቹ ከጥፋታቸው ይመለሱ ዘንድ ከመናገር ፥ ከማጋለጥ እና ህዝብን ከማሳወቅ ዝም አንልም ፥ የገደዳቸው የፖለቲካ ሂሳቡ ምናባዊ ( complex imaginery ) ሲሆንባቸው የተሻለ የምንለውን እንናገራለን ። ቢያንስ ቢያንስ የምንኖርበት ሃገር ታሪክ ፥ የዕለት ተዕለት የህይወት ሂደቱ ( ውጣ ውረዱ ) የሚያሳየን እሱን ነው ። ትሞክራለህ ፥ ይበላሽብሃል ፥ ደግመህ ትሞክራል ፥ አሁንም አልሰራም ይልሃል ፥ ትገመገማለህ ፥ ሙከራውን ወደሚሰራ አቅጣጫ ሊወስድ የሚያስችል አቅም የነጠፍክ ከሆነ የተሻለ ይመለመላል ። ትግል እምነት አይደለም ። እምነት ላይ ክርስቶስ አለ እሱን ሲከተል ኖሮ አርጅቶ የሚሞት ትውልድ አለ ፥ ለአዲሱ ትውልድም ያው የቅድሙ ( የቀደመው ) ክርስቶስ አለ ። ይህ የሚመረመር ፥ የሚፈተን ፥ የሚጠየቅ ነገር ስላይደለ « ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው » የሚለውን እያነበብክ ፥ ተስፋ እና ፍቅር ሰንቀህ ፥ አምነህ ትኖራለህ ። ፖለቲካ ግን እንዲያ አይደለም ። ፖለቲካ የመሪዎች ታሪክ ነው ለዚህም ነው ታላቁ ሆመር በጣፈው ኢሊያድ ላይ

<< history remember kings but not soldiers>> የሚለው ። ስለዚህ ስለ ክሽፈት ስናወራ ከመሪ ጋ ይያያዛል ማለት ነው ። መሪዎች መስማትም መቀበልም ያለባቸው ነገር አለ ስንል ከዚህ ተነስተን ነው ። ውድቀቱም ሆነ ድሉ መጀመሪያ የነሱ ነውና !

ለምሳሌ ጦርነቱን ለማሸነፍ በግለሰብ ደረጃም ቢሆን ወርደው ማሰብ የሚጠቅም ከሆነ ማድረግ ። የቡድን አስተሳሰብ ካልሰራ በግለሰብ ደረጃም ቢሆን የሚሰራ ሃሳብ መፍጠር ። በኢሊያድ ላይ ኦዳይሰስ እና አገማምኖን ይህንን ብለው ነበር

Agamemnon: Achilles is one man!
Odysseus: Hector is one man! Look what he did to us today!
Agamemnon: Hector fights for his country! Achilles fights only for himself!
Odysseus: I don’t care about the man’s allegiance, I care about his ability to win battles!

በዘራቸው ሳይሆን በችሎታቸው ጦር ሊመሩ የሚችሉ ታጋዮችን ማቀፍ ፥ ማሳተፍ እና ወደፊት ማምጣት ወሳኝ ነው ። እንዳንናገር የምትፈልጉትን አካሎች ግን ” በእርግጥ እኛ እናንተን ኣይደለንም !” እንናገራለን !! ለውጥ እስኪመጣ ድረስ! መናገር የሚጎዳውን ትግል ፥ ዝምታ አያድነውም!!!! ሹክሹክታ እንዲያገግም አያደርገውም ። የጀርባ ወሬ አያተርፈውም ። እንደውም የሚገለው እሱ ነው !