የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ነኝ ባዩ ዮሃንስ ሳህሌ በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ከባድ ዘረፋ ፈጽሟል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ነኝ ባዩ አቶ ዮሀንስ ሳህሌ 10 ወራት ብቻ ቆይቷል። በአጠቃላይ 25 ጨዋታዎችን በአሰልጣኝነት መርቶ ከ 630ሺ ብር በላይ ተቀብሏል። የተጣራ 50ሺ የወር ደመወዝ፣ 55,000 የኢንተርናሽናል ስልክ ወጪ፣ 27,500 የመኪና ነዳጅ ሲደማመር 632,500 ብር ተከፍሎት ከሃላፊነቱ እንዲለቅ ተደርጓል፡፡ ይህ ሁሉ ገንዘብ በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አጭበርብሮ የተከፈለው ነው። አሁን ጥያቄው ይህን ሰው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን “በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተጭበርብሬያለሁ” ብሎ ለፍርድ ያቀርበዋል ወይስ ባላየ ያልፈዋል የሚለው ነው። በቅርቡ በእግር ኳስ ፌድሬሽን እና በካፍ መካከል በተደረገ ኢሜይል ልውውጥ ዮሀንስን በኢንስትራክተርነት አናውቀውም የሚሉ ዘገባዎች በሚዲያዎች እና በማህበራ ድረገጽ በስፋት ሲደመጡ ተስተውለዋል::