ከጋምቤላ ታፍነው የተወሰዱት ሕጻናት በገንዘብ ለማስለቀቅ ድርድር ተይዟል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ባለፈው ሳምንት ከደቡብ ሱዳን ድንበሩን አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ የጋምቤላ ክልል በመግባት በርካቶችን በመግደል ታዳጊ ሕጻናትን አፍነው የወሰዱት ታጣቂዎች አፍነው የወሰዷቸውን ታዳጊዎች በጆንግሌ ግዛት ዋት ተብሎ በሚጠራ አከባቢ አስፍረዋቸው ከደቡብ ሱዳን መግስት እና ከኢሕኣዴግ አገዛዝ ጋር እየተደራደሩ መሆኑን አዲስ አበባ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ ዲፕሎማቲክ ምንጮች ተናግረዋል::
የኢሕአዴግ አገዛዝ የመከላከያ ሰራዊቴ ሕጻናቱ ያሉበትን ቦታ ከቧል አስለቅቋል የሚለውን ፕሮፓጋንዳ ያናፈሰ ቢሆንም በወቅቱ በአከባቢው እንቀሳቀሳለን የሚሉ ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ድርጅት አባላቶች ምንም አይነት የመከላከያ ሰራዊት ይሁን የጦር ሃይል አለመኖሩት የተናገሩ ሲሆን የደቡብ ሱዳን የአዲስ አበባ ኤምባሲ ዲፕሎማቶችም ለምንሊክ ሳልሳዊ ይህንን አረጋግጠዋል:: አንድ ጊዝኣ ከበላ አንድ ጊዜ አስለቅቀናል የሚለው የኢትዮጵያ መንግስት ዜና አፋዊ ሲሆን ዲፕሎማቶቹ እንዳሉ የኢትዮጵያ መንግስት የመከላከያ ሰራዊት ተጣቂዎችን መክበብ አይደለም ወደ ድንበርም አልተጠጋም በማለት ተናግረዋል::
ታጣቂዎቹ የሚደገፉት በሪክ ማቻር ነው የሚሉት ዲፕሎማቶቹ የደቡብ ሱዳንን የሰላም ሂደት ለማደፍረስ የሚደረግ ሴራ አካል መሆኑን በመግለጽ በሪክ ማቻር እና በጋምቤላ ክልል ርእሰ መስተዳደር ላይ የጋምቤላ ሕዝብ ያደረገው ተቃውሞን ጠቅሰዋል::ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተል የኢሕኣዴግ የውጪ ጉዳይ ሰራተኛ እንደሚለው የሕወሓት ሰዎች እና የሰሜን ሱዳን ለሪክ ማቻር ድጋፍ የሚያደርጉ ሲሆን በጋምቤላ ክልል የተፈጸመው ግድያ እና አፈና የፈጸሙት ደግሞ በሪክ ማቻር የሚደገፉ ሃይሎች ናቸው ሲሉ ይወነጅላሉ::ከጋምቤላ ክልል ታፍነው የተወሰዱ ሕጻናትን ገንዘብ ከፍሎ ለማስለቀቅ ድርድሩ ቀጥሏል::ድርድሩ ካልተሳካ ሕጻናቱ ያላቸው እድል ለአማጽያን በወታደርነት እንዲያገለግሉ ይሸጣሉ የሚል መረጃ ተገኝቷል::#ምንሊክሳልሳዊ
