ሰበር ዜና: – አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) (የእምነት ክህደት ቃል ) ከነገ ጀምሮ ዲሲ ፍርድ ቤት ይሰጣሉ።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
(አዲስ መረጃ ተካቷል ) ሚያዚያ 3 ቀን 2008 ዓ.ም. (April 11, 2016)

አቡነ ፋኑኤል የፓትርያርክ አርዌ ብርት ይዘው ይታያሉ። የሚገርመው በስራቸው ያሉ መነኮሳቱ ሁሉ ይህንን ተቅብሎ አብሮ ‘ያሸረግዳሉ’።
ይህንን ጉዳይ እየተከታተልን አዳዲስ መረጃዎችን እናቀርባለን ባልነው መሰረት አሁን የደረሰን አዲስ መረጃ እንደሚያመለከተው የከሳሽ ወገን ጠበቃ ጥያቄዬን ጨርሻለሁ ብሎ እስኪያበቃ ድረስ የእምነት ክህደት ቃል በተከታታይ ብዙ ቀናት ሊቆይ የሚችል እንደሚሆን መረጃው ያሳያል።(አቡነ ፋኑኤል ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የከሳሽ ጠበቃ ያለ ሰዓት ገደብ የሚፈልገው ጥያቄ እንዲጠይቅ የታዘዙበት የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ):: ቀደም ብሎ የዘገብነውን ቀጥሎ ማየት ይቻላል።
ስለፍርድ ቤቱ ቀጠሮ የሚቀጥለውን ይመልከቱ። http://www.mereja.com/amharic/490212
ስትንሽ ስለ አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) አዋናባጅነት ከዜና ማህደራችን- ቀጥሎ ይመልከቱ። http://www.mereja.com/amharic/491127