በሼህ ሆጀሌ መስጂድ ሙስሊሞች በፖሊሶች ተደበደቡ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ለኢሻ ሰላት በሼህ ሆጀሌ መስጂድ ተገኝተው የነበሩ የተወነሱ ሙስሊሞች በፖሊሶች ተደበደቡ

አቡ ዳውድ ኡስማን

ትላንት መጋቢት 2 /2008 ከኢሻ ሰላት በኋላ በታላቁ ሼህ ሆጀሌ መስጂድ ፖሊሶች ወደ መስጂዱ በመግባት በመስጂዱ የነበሩትን የተወሰኑ ሙስሊሞች ደብድበዋቸዋል፡፡

በተደጋጋሚ በመስጂዱ ረብሻ ፈጥሮ ሙሰሊሙን በመደብደብ ለማሸማቀቅ ጥረት ሲያደርጉ የከረሙት እነዚህ ፀረ ሰላም ሃይሎች ያሰቡት ረብሻ እና ትንኮሳ ሊሳካላቸው ባለመቻሉ እራሳቸው ዘዴ በመፍጠር ኢሻ ሰላት ተሰግዶ ከተጠናቀቀ በኋላ በመስጂዱ ቀርተው የነበሩ የተወሰኑ ሙስሊሞችን በፖሊስ እንዲደበደቡ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡

በአህባሽ መጅሊሱ ከተቀጠሩት ዘበኞች መካከል አንዱ በመስጂዱ በሴቶች በኩል የመስጂዱ መጋዘኑ አካባቢ በመሆን ማንም አጠገቡ በሌለበት ሁኔታ ሆን ብሎ አውቆ ሰው እየደበደበው እንደሆነ አስመስሎ የድረሱልኝ ጥሪ በማሰማት የጮኸ ሲሆን በመስጂዱ ዙሪያ ዘበኛው ጩኸቱን እስኪያሰማ ሲጠባበቁ የነበሩ ሙስሊሙን ለመደብደብ የተዘጋጁት ፖሊሶችም ወደ መስጂዱ በመግባት ከኢሻ ሰላት በኋላ በመስጂዱ ቀርተው የነበሩ ሙስሊሞችን ደብድበዋቸዋል፡፡

የተወሰኑትን ወጣቶችም ወደ ፖሊስ ጣብያ ይዘዋቸው የሄዱ ሲሆን እነዚህ ፀረ ሰላም ሃይሎች ይህን የተቀነባባረ ድብደባ የፈፀሙት በመስጂዱ ከዚህ ቡኋላ አህባሾችለሚያደርጉት እንቅስቃሴ የአካባቢው ሙስሊም ፈርቶ እንዳይቀወማቸው ለማሰደንገጥ መሆኑ ታውቋል፡፡

አህባሾቹ የመስጂዱን ቁልፎች በሙሉ በራሳቸው አዲስ ቁልፍ የቀየሩት ሲሆን አዲስ የጥበቃ ሰራተኛ እና ጫካ ጠባቂ የነበረ ግለሰብም የመስጂዱ አስተዳደር አድረገው ቀጥረዋል፡፡

ዋ ኢስላማ

ሃስቡን አላህ ወኒ አመል ወኪል

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
ወቅታዊ መረጃዎችን እና ኢስላማዊ ትምህርቶችን ለማግኘት ይህን ገፅ ላይክ ያድርጉ
Click and Like ➤➤ @ https://www.facebook.com/abudawdosman
Click and Like ➤➤ @ https://www.facebook.com/abudawdosman

Abu Dawd Osman's photo.