በቫይቨርና ዋትስአፕ ላይ የክፍያ እቅድ – ዶይቸ ቬለ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጭ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ሰሞኑን በቫይበር፣ በዋትስ አፕና መሰል የድምፅ ጥሪ አገልግሎቶች መስጫዎች ላይ ክፍያ ለመጠየቅ እንዳቀደ የኩባንያዉ የሥራ አመራር ለተለያዩ ሚዲያዎች መናገራቸዉ ይታወቃል።
በእነዚህ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች ላይ ክፍያ ለመጣል የታሰበበት ምክንያት፤ መንግስት ማገኘት የሚችለዉን ከፍተኛ ገቢ ሳያገኝ በመቅረቱና ይህንኑ ቴክኖሎጂ ተጠቅመዉ ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን የሚፈፅሙትን ለመቆጣጠር እንደሆነ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ኢትዮ ቴሌኮም ክፍያዉን ለማስፈፀምና እንደተባለዉ ተያየዥ የሕገ-ወጥ ሥራዎችን ለመቆጣጠር «ፖሊሲ ቻርጅ ኤንድ ኮንትሮል ሲስተም» የሚባል አዲስ ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀም የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስካያጅ አቶ አንዱአለም አድማሴ መናገራቸዉ ተዘግቧል።
ይህ ቴክኖሎጂ የቫይቤርም ሆነ ዋትስ አፕ አገልግሎት አንድ ሰዉ ሲጠቀም የሚያሰገባዉ ስልክ ቁጥር በኢትዮ ቴሌኮም ኔትዎርክ ተጠቅሞ በመሆኑ፤ በዚህ ዉስጥ ሲያልፍ ክፍያዉን ያስፈፅማል ሲሉ የእንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዉ አቶ ማርቆስ ለማ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። አቶ ማርቆስ ይህ ርምጃ የቴኪኖሎጂዉ ተጠቃሚ ላይ የሚያመጣዉ ተፅእኖ እንዳለም ሳይጠቅሱ አለለፉም።
ይህ የኢትዮ-ቴሌኮም ርምጃ ሃገሪቱ ዉስጥ በሚካሄዱት ሕዝባዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችም ሆነ የኤኮኖሚ ዉይይቶች ላይ ተጽእኖ ቢኖረዉም በፌስ ቡክ ማህበራዊ ግኑኝነቶችና አገልግሎት ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ እንደሌለዉ ማርቆስ ይናገራሉ።
ይሁን እንጂ ተጠቃሚዎች ይህ ኢትዮ ቴሌኮም ርምጃ አፈና ነዉ ሲሉ አሳባቸዉን የሚገልፁ ጥቂት አይደሉም። አዲስ አበባ ፒያሳ አከባቢ ነዋሪ የሆኑት አቶ ተስፋዬ መርኔ እንዳሉት፤ አንዱ ለግልጋሎት በነፃ የለቀቀዉን፤ ሌላዉ የአገልግሎት ክፍያ መጠየቁን ተችተዋል። ለማፈኛ እንጅ የኢትዮ ቴሌኮም ገቢ የማጣት ሥጋት ምክንያት ሆኖ እንዳልሆነም ይናገራሉ።
ሌላዉ የተክለሃይማኖት አከባቢ ነዋሪ አቶ ካሳሁን በርይሁን በበኩላቸዉ ገና ይሄን ዜና ስሰማ መንግሥት ለማፈኛ ሊመጠቀም እንደሆነ ገብቶኛል ሲሉ ነዉ የገለፁልን። መንግሥት ገቢ አጣሁ ብሎ እነዚህ አገልግሎቶች ላይ ርምጃ ከመዉሰድ በሕገ-ወጥ ስልክ ማስደወል ሥራ ላይ የተሰማሩትን መቆጣጠር አለበት ስሉ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል። ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ →listen