የትግራይ ወጣት ልቡ ሸፍተዋል :: ……ህወሓት
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
“የትግራይ ወጣት ልቡ ሸፍተዋል”……ህወሓት
“የትግራይ ወጣት ልቡ ሸፍተዋል በተለይ ፌስቡክ የሚጠቀም ከ እኛ(ህወሓት) ርቆ ሂደዋል” የሚል ድምዳሜ የቀረበው በመቐለ ከተማ በተካሄደው የዞኑ የወጣቶች ኮንፈረስ ነው።
የህወሓት መሪዎች ሰሞኑን የመቐለ ወጣት የባጃጅ ሹፌሮች ለኣራት ቀናት በማመፃቸው ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠረባቸው ሲሆን፡ ለወጣቱ ደግሞ በህወሓት ላይ ሲከተለው የነበረው ዝምታው ሰብሮለታል።
የወጣቶች ኮንፈረሱ ቅዳሜና እሁድ (17ና 18/07 2008 ዓ/ም) በመላ የትግራይ ዞኖች እየተካሄደ ያለው የወጣቶች የመልካም አስተዳድር ኮንፈረንስ ኣካል ነው።
በመቐለ ዞን እየተካሄደ ባለው የወጣቶች ኮንፈረንስ ህወሓት ወጣቱ ትውልድ “ሽፍታ” የሚል ቀሚስ ሰጥታዋለች።
ህወሓት በምርጫ 97 የተነሳው የወጣት የለውጥ ፍላጎትና ተነሳሽነት “ኣደገኛ ቦዘኔ” የሚል ቅጥያ ለጥፎባቸው ነበር።
ኣዎ … ! የመቐለ ፣ የትግራይ በህወሓት ላይ ልቡ ሸፍተዋል ።
ወጣቶቹ ልባቸው ከሽፍትነት ወደ ተደራጀ ሰለማዊ ትግል ሲያሸጋግረው ደግሞ እንደ ኣብራሃ ደስታ፣ ቐሺ ብርሃኑ ቖባዕ፣ ወይዘሮ ኣልጋነሽ ገብሩና ሌሎች ሰላማዊ ታጋዮች “ኣሸባሪነት” የሚል ካባ ሊጭንባቸው ይችላል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
it is so.
