የመሃል አገሩ ዝምታ እስከመቼ ነው ? – የህዝብ ማእበል = የትጥቅ ትግል = ካልደፈረሰ አይጠራም !!!


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የመሃል አገሩ ዝምታ እስከመቼ ነው ? – የህዝብ ማእበል = የትጥቅ ትግል = ካልደፈረሰ አይጠራም !!!
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎AddisAbaba‬ ‪#‎Ethiopianoppositionparties‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

ኢሕአዴግ ሃብትና ሥልጣንን ለሕዝብ አያጋራም። ሁሌም የበላይ ሆኖ ሌሎችን መምራትና መቆጣጠር ብቻ ነው የሚፈልገው። ሌሎቹ እሱን እንዲያጅቡት ነው እቅዱ። ለሚቀጥሉት ብዙ ዓመታትም ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ለመታየት የሚያስችለውን እርምጃ ሁሉ ከመውሰድ አይመለስም። ኢሕአዴግ ገንዘብ ያላቸውን ዓለም አቀፍ ዘራፊዎች የሚሰበስበው፣ ከትላልቅ ሃገራት የጸጥታ ድርጅቶች ጋር የሚሰራው፣ ከአለም አቀፍ አሸብር እና ወንጀለኛ ድርጅቶች ጋር በጋራ የሚንቀሳቀሰው ፣ ሰላማዊ ዜጎችን እያፈሰ በአሸባርነት የሚወነጅለው ፣ ገንዘብ እየረጨ በየመንደሩ የራሱን ሚሊዮነር የሚቀፈቅፈውና ሰራዊቱን የሚያንጸው ለሃገር ብሎ አይደለም። ለአንድ ግልጽ ዓላማ ነው፤ ሥልጣኑን ላለማጋራት፤ ሥልጣን አጠገብ ሕዝብን ላለማድረስ! …..ያ መታመን ያለበት እውነት ነው። ይህንን ማመን ከቻልን ስልጣን የሕዝብ እስከሆነ ድረስ እኛ ህዝቦች ስልጣናችንን በጃችን ለማስገባት በትግሉ መስክ መፈንቀል ያለበትን ሁሉ መፈንቀል አለብን – ሕዝባዊ ማእበል ።

በምንም ተአምር አትታለሉ፤ ኢሕአዴግ በምንም ሁኔታ ለሕዝብ ሥልጣኑን አሳልፎ ለማንም አይሰጥም። ከተለያዩ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የፈለገ ዓይነት ስምምንነት ቢያደርግ፣ ለለውጥ ሃይሎች ሥልጣኑን ያጋራል ማለት አይደለም። ቁራሽ ሥልጣን ቁርሽ ለውጥ ጠብቃችሁ ከሆነ ዳግም ተሞኝታችኋል። በዚህ አጋጣሚ ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር በሽብር የታወቀው ሕወሓት ከወደቀ የብአዴን እና ኦሕዴድ በህይወት መኖር ያበቃለታል።ለዚህ ደሞ ከትግሉ እርምጃዎች ጋራ አባሪ ተነባባሪ ሆነን ከትጉ በመቀላቀል መስራት ወቅቱ አሁን ነው።

ከኢሕአዴግ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የጠበቃችሁ፤ ከኢሕአዴግ ሥልጣን መጋራት የፈለጋችሁ፤ ከኢሕአዴግ የእምነት፣ የፕሬስና የሃሳብ ነጻነት የጓጓችሁ፤ ‘ከኢሕአዴግ ጋር ተስማምቶ መሥራት ይቻላል’ የምትሉ፤ ተስፋ ቁረጡ። እንኳን አብሮ ለመሥራት ለመወዳደር እድል የማይሰጥ ፈሪ ድርጅት መሆኑን በይፋ አረጋግጧል። ከኢሕአዴግ ጋር አንድ ነገር ብቻ ነው የሚቻለው፤ ከኢሕአዴግ በታች ሆኖ መሥራት። ጫማ እየላሱ ‘ጌታዬ!’ ማለት። ያንን የሚመርጥ የፖለቲካ ድርጅት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደፈለገ መንቀሳቀስና መሥራት ይችላል። ጥሩ ቢሮ ይሰጠዋል። ግዙፍ ባጀት ይመደብለታል። ዓመታዊ ጉባዔውን ሼራተን መደገስ ይችላል። በየምክንያቱ ቤተመንግሥት መግባት መብቱ ይሆናል። የመገናኛ ብዙሃን ችግር አይገጥመውም። እስር፣ ዛቻና ወከባ ሕልም ሆነው ይቀሩለታል። ‘ባሪያ የተቃዋሚ ድርጅት’ እየተባለም ይወደሳል።እንዲህ አይነት አደርባይነትን እና የህዝብን የለውጥ ጥያቂ ለሆዳቸው የሚጠቀሙበትን ፖለቲከኞች ድባቅ በመምታት በአጭሩ ለመቅጨት በጋራ እንታገል።

ስለዚህ እያንዳንዳችን ኢሕአደግን ወደ ከርሰ መቃብር ለመክተት በህዝባዊ ማእበል እና በትጥቅ ትግል በሙሉ ሃይል ተባብሮ በመታገል የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነት ማረጋገጥ የእያንዳንዳችን ሃላፊነት እና ድርሻ መሆኑን መገንዘብ ግደታችን ነው። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!! ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.