የነፃነት ትግላችን ዋነኛ ምሰሶ ለነፃነታችን በፈቃደኝነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናችን ነው። ማዲባ (Natnail Feleke)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


<<የነፃነት ትግላችን ዋነኛ ምሰሶ ለነፃነታችን በፈቃደኝነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናችን ነው።>>  ማዲባ “Long walk to Freedom”

(Natnail Feleke= Zone 9 )

አንዳንዴ <<ተስፋ>> ጠላታችን ይሆናል። ነገሮች እንደሚሻሻሉ ወይንም ከዚህ የባሰ እንዳይከፉ እያልን በተስፋ እየተታለልን ማድረግ የሚገባንን ሳናደርግ ወደን ሳይሆን ተገደን እንከፍላለን። ነፃነታችንን የሚያጎናፅፈን መክፈል ብቻ ሳይሆን የምንከፍለው ለነፃነት የሚገባውን መሆኑን አምነን በፈቃደኝነት ወደን ስንከፍል ነው።

አምባገነኖች በሚያስተዳድሯት ሀገር ተራ በተራ እያንዳንዳችን ላይ የጭቆና በትር ማረፉ አይቀርም። ጥያቄው እየሸሸንም ቢሆን ተራችንን ጠብቀን ዋጋ ከፍለን ጭቆናን እናራዝማለን ወይንስ በፈቃደኝነት ዋጋ ከፍለን ነፃነታችንን እንጎናፀፋለን? ነው።

ከዕስር ከመውጣታችን በፊት ለነፃነቴ መከፈል ከሚገባው ዋጋ ላይ እየቀነስኩኝ ነበር። እያንዳንዷ በዕስር የማሳልፋት ቀን ለነፃነቴ እያቀረበችኝ እንደሆነ ነበር የሚሰማኝ።

ከዕስር ከወጣሁ በኋላ ለነፃነቴ ለመክፈል ያለኝ ፈቃደኝነት በብዙ <<ምክንያቶች>> አብሮኝ የለም።

ወዳጄ የሺዋስ አሰፋ <<ፍርሃት በብዙ ምክንያቶች ተሽሞንሙና ትደበቃለች>> ይለኝ ነበር። ምናልባት ማረሚያ ቤት ካገኘሁት ዓይኑን እንዴት እንደማይ አላውቅም።

ይህች ጽሑፍ ምናልባት በራሴ የፌስቡክ ግርግዳ ላይ የማሰፍራት የመጨረሻ ልትሆን ትችላለች። የፊታችን ማክሰኞ መጋቢት 20 ቀን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ላይ የሚሰጠውን ውሳኔ ለመስማት ዳኞች ፊት ከጓደኞቼ ጋር እቆማለሁ። ተራዬ ደርሶ (ሁለተኛ?) የጭቆና በትር ይሰነዘርብኝ ይሆናል። ወይንም እንደገና <<ተስፋ>> ለማድረግ እቀጠር ይሆናል።

ለክፉም ለደጉም እስር ቤት ያስተዋወቀኝን አንድ ምርጥ ጸሐፊ ልጥቀስ እና የኔ ጉዳይ ለሚያሳስባችሁ ሰዎች ማልቀሻ ልተውላችሁ:–

“…And if it is a despot you would dethrone, see first that his throne erected within you is destroyed.

“For how can a tyrant rule the free and the proud, but for a tyranny in their own freedom and a shame in their own pride?

“And if it is a care you would cast off, that care has been chosen by you rather than imposed upon you.

“And if it is a fear you would dispel, the seat of that fear is in your heart and not in the hand of the feared.”

Kahlil Gibran, The Prophet