በደቡብ ኦሞ የእነ አቶ ዓለማዬሁ እስራት ‹‹ ከአርበኞች ግንቦት 7 ›› ጋር ግንኑነት አላቸው በሚል ጥርጣሬ ነው::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በደቡብ ኦሞ የእነ አቶ ዓለማዬሁ እስራት ‹‹ ከአርበኞች ግንቦት 7 ›› ጋር የተያያዘ ነው//
‹‹ አይ ፍርሃት– ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ሲያንከራትት›› ከሰዐት በፊት ባቀረብነው መረጃ የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ም/ሊቀመንበር አቶ ዓለማዬሁ መኮንን፣ አንድ ጠንካራ አባልና አንድ የከተማው ነዋሪ ቤት ተፈትሾ መታሰራችውን ገልጸናል፡፡ አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት የእስራቱ መነሻ ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኑነት አላቸው በሚል ጥርጣሬ እንደሆነ ፖሊስ ለፍተሸ ከፍርድ ቤት ካወታው ትዕዛዝ ማወቅ ተችሏል፡፡
በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት-እንዲፈተሹ የተባሉት–1. የኤሌክትሪኒክስ መሳሪያዎች፣ 2. የአርበኞች ግንቦት 7 ወረቀቶች ፣3. ጦር መሳሪያ ሲሆኑ
በዚሁ ፍተሻ ከተጠርጣሪዎቹ ቤቶች የተወሰዱ ዕቃዎች ዝርዝር
1. ከአቶ ዓለማዬሁ መኖሪያ ቤት፡- 1.1. የአቶ ዓለማዬሁ ሁዋይ ሞባይል ስልክ 1.2. የባለቤታቸው እንከንየለሽ ታደለ ሶኒ ሞባይል 1.3. ሶኒ ዲጂታል ካሜራ 1.4. ስድስት/6/ የመዝሙር ካሴቶች 1.5. ዘጠኝ /9/ የቪዲዮ ካሴቶች/ስድስቱ የት/ቤት ጉብኝት / 1.6. አራት/4/ የፎቶግራፍ ፍልሞች 1.7. ሰባት/7/ ገጽ ለኤዲት የተሰጡት ሁለት ግጥሞች– ‹ለአምላኬ ልንገረው › እና ‹ ይብቃን ዝምታው› ርዕስ የተጻፉ (አቶ ዓለማዬሁ የመሰናዶ ት/ቤት የቋንቋ-እንግሊዘኛ መምህር ናቸው) 1.8. አምስት/5/ ገጽ በሳላማጎ ወረዳና በኮንሶ ተቃውሞዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ስም ዝርዝርና መረጃ የያዘ ማስታወሻ ፤
2. ከአቶ አብርሃም ብዙነህ ቤት፡- 2.1. ሞባይል ስልክ 2.2. አንድ ገጽ ‹‹ የኦሮሞ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የኢትዮጵያ ህዝብ አስቡት›› የሚል ወረቀት፣ 2.3. የኢትዮጵያ ባንዲራ ስትኬር /ቀይ፣፣ቢጫ ፣አረንጓዴ /፣
3. ከአቶ ስለሺ ጌታቸው ፡- 3.1. ሞባይል፣ 3.2. የልጃቸው የአካል ስለሺ ላፕቶፕ፣ ሲሆን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ የተሰጠው በ3ቱ ተጠርጣሪዎች ቤት ላይ ሆኖ እያለ ከአቶ ስለሺ ቤት ቢያንስ 400 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው እናታቸው የወ/ሮ ጥሩነሽ ጌታሁን ቤት ያለትእዛዝ እንደተፈተሸ የደረሰን መረጃ ያሳያል፡፡
በቀደመው መረጃ አቶ ስለሺ ‹ሊሊ ግሮሰሪ› ከፖሊስ ጋር መታየታቸው እውነት ሲሆን የተገኙትም ግሮሰሪው አጠገብ በሚገኘው በአቶ ጃራ ኤሌክትሮኒክስ ቤት ሞባይላቸውን ለማስከፈትና ለመፈተሸ ባለሙያ እየጠበቁ መሆኑ ተገልጧል፡፡ ለካስ መፍራት ሲጀመር የመዝሙር ካሴትና ወረቀትም ያስፈራልና// የህወኃት/ኢህአዴግ መንግስት ሆይ በሚያስፈራውም በማያስፈራውም እየደነበርክ የቆቅ ህይወት (ከተባለ) ከመግፋት፣ ይህ ዓይነቱ ስጋትም ሆነ በአፈሙዝ በመግደል፣አካል በማጉደልም ሆነ በማስፈራራት የህዝብን ጥያቄና ተቃውሞ ማፈን ጊዜው አልፎበታልና ለህዝብ ጥያቄዎች ህገመንግስታዊ ምላሽ በመስጠት ከማንም በላይ ተጠቃሚ ሁን መልእክታችን ነው፡፡ ለአገራችንና ህዝቧ ደግ ገዱን ያሰማን፡፡