ይግባኝ የተጠየቀባቸው የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን መጋቢት 20 ለብይን ጠቅላይ ፍ/ቤት ይቀርባሉ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Mahlet Fantahun Tefera's photo.

ይግባኝ የተጠየቀባቸው የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን መጋቢት 20 ለብይን ጠቅላይ ፍ/ቤት ይቀርባሉ
★★★★
በእነ ሶሊያና ሽመልስ መዝገብ ህብረተሰብን አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሳችኋል በመባል በፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ 4 ክስ ከተመሰረተብን ሰባት የዞን 9 ጦማሪያን እና ሶስት ጋዜጠኞች ውስጥ የአምስቱ ክስ ተቋርጦ፣ አራቱ በነፃ እንዲሁም አንዱ (ጦማሪ በፍቃዱ ሐይሉ) አንቀፅ ተቀይሮ እንዲከላከል ተወስኖ፤ ለአመት ከስድስት ወር ጊዜ በእስር ሆነን ክሳችንን ስንከታተል ከቆየን በኃላ ሁላችንም ከእስር ቤት ወጥተናል። ከእስር ቤት ብንወጣም ከእስር የማይተናነስ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው። ወደቀድሞ ስራችን መመለስ አልቻልንም፣ አዲስ ስራ ለማግኘት ተቸግረናል፣ ወደ ሌላ ሃገራት ለመጓዝ ስንሞክር በኢምግሬሽን መ/ቤት ፓስፓርታችንን ተቀምተን እንዳንወጣ እንታገዳለን .. ሌላም ሌላም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ስር ፍርድቤት (ከፍተኛ 19ኛ ችሎት) ነፃ ናቸው ብሎ ያሰናበታቸውን አምስት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን (ሶሊያና ሽመልስ /በሌለችበት/፣ በፍቃዱ ሃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፍ ብርሃኔ እና አቤል ዋበላ) አቃቢ ህግ ይግባኝ ብሎባቸው ጠቅላይ ፍርድ ቤት መካሄድ ያለበት ክርክር በባለፈው ቀጠሮ ተጠናቋል ። ዳኞችም ክርክሩን መርምረው “መከላከል የለባቸውም ወይም አለባቸው” የሚል ብይን ለመስጠት ለመጪው መጋቢት 20/ 2008 ቀጠሮ ሰጥተዋል። በተከሰሱበት አንቀፅ እንዲከላከሉ ብይን ከተሰጠ ዳግም በእስር ቤት ሆነው ይሆናል ድራማውን የሚቀጥሉት።