ሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም በእርስ በእርስ ጦርነት ልትታመስ ነው::የወልቃይት ሕዝብ ዱር ቤቴ ብሏል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም በእርስ በእርስ ጦርነት ልትታመስ ነው::የወልቃይት ሕዝብ ዱር ቤቴ ብሏል:: #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል እና በአማራ ክልል መካከል ያለውን ድንበር የሕወሓት አምባገነን አገዛዝ ዘልቆ በመግባት ወደ ትግራይ ክልል በሃይል በማካለሉ የመጠ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ያነሳው የማንነት ጥያቄ መልስ ባለማግኘቱ የሕወሓት አገዛዝ የወልቃይት ነዋሪዎችን ትግሬዎች ናችሁ ብሎ ለማስገደድ ሲሞክር አይደለንም አማራ ነን በሚል በተከሰተ አለመግባባት የሕወሓት አገዛዝ ጦሩን ሰብቆ ሕዝቡን በመዳፈሩ እና የአከባቢው ስለጉዳዩ ሽምግልና የተመረጡ ነዋሪዎችን አፍኖ በመውሰዱ የመጣ የወልቃይት ሕዝብ ዱር ቤቴ ብሉ መስሪያውን ወልውሎ ወደ ጫካ መውረዱ ታውቋል::
የወልቃይት ሕዝብ ጫካ መግባቱን ተከትሎ የዳንሻ እና ሶሮቃ ከተሞች ከቀድሞው በበለጠ በወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ዙሪያዋን ታጥራ ስትገኝ በአከባቢው የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የተቋረጠ መሆኑ ሲታወቅ ሰውም ይሁን መኪኖች ወደ ከተማው እንዳይገቡ እንዳይወጡ ተደርጓል:: በከተማዋ የፌዴራል ፖሊስ እና ሚሊሻዎች አሰሳ በማድረግ ያገኙትን ሰዎች ሁሉ እያፈሱ ወደ ትግራይ በመውሰድ እያሰሩ ይገኛሉ::