እውን በሕገወጥ መንገድ በባለስልጣናት እና በዘመዶቻቸው በደላሎቻቸውና ወዳጆቻቸው የተያዙት ቤቶች 98 ብቻ ናቸውን ?


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


እውን በሕገወጥ መንገድ በባለስልጣናት እና በዘመዶቻቸው በደላሎቻቸውና ወዳጆቻቸው የተያዙት ቤቶች 98 ብቻ ናቸውን ? mereja.com

በሕገወጥ መንገድ 98 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ሰብረው የያዙ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ Reporter amharic

እየተካሄደ ባለው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ቆጠራ 98 ቤቶች በሕገወጥ መንገድ የተያዙ መሆናቸው በመረጋገጡ፣ በሕገወጥነት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡

እስከ ዓርብ መጋቢት 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ 94,101 ቤቶች መቆጠራቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ቆጠራው መጋቢት 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡

በሕገወጥ መንገድ የተያዙት ቤቶች በአብዛኛው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ናቸው፡፡ ግለሰቦቹ ቤቶቹን ሰብረው በመግባት መኖር የጀመሩ፣ የሚያከራዩ፣ ከራሳቸው ቤት ጋር ቀላቅለው የያዙ እንደሆኑ የአዲስ አበባ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

እነዚህ ሕገወጥ ተግባር የተፈጸመባቸው ቤቶች ለልማት ተነሽዎች ተብለው የተቀመጡ ነበሩ፡፡ ለልማት ተነሽዎች ለመስጠት በሚታሰብበት ወቅት አብዛኛዎቹ የልማት ተነሽዎች ፍላጎት ባለ ሁለትና ባለ ሦስት መኝታዎች በመሆኑና እነዚህ ቤቶች ደግሞ ስቱዲዮና ባለ አንድ መኝታ በመሆናቸው ያለ አገልግሎት ተቀምጠው ነበር፡፡

ቤቶቹ ባዷቸውን በመቀመጣቸው ለሕገወጥ አገልግሎት የዋሉ በመሆኑና አስተዳደሩም ሕግ ማስከበር ስላለበት ዕርምጃ መውሰዱን አቶ ይድነቃቸው ተናግረዋል፡፡

ለልማት ተነሽዎች ተብሎ ባዷቸውን ተቀምጠው ከነበሩ ከስምንት ሺሕ በላይ ቤቶች ውስጥ እስካሁን 1,200 የሚሆኑት በነበሩበት ተገኝተዋል ተብሏል፡፡

ቆጠራው ሙሉ በሙሉ ከተጠናቀቀ በኋላ በሕገወጦቹ ላይ የሚወሰደው ዕርምጃ ይፋ እንደሚሆን አቶ ይድነቃቸው ተናግረዋል፡፡

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ከዕጣ ውጪ በሌላ መንገድ ሊተላለፉ ስለማይችሉ እጅግ መጠነ ሰፊ የቤት ችግር ባለባት አዲስ አበባ፣ እነዚህ ቤቶች ያለተጠቃሚ እንዲቆዩ መደረጉን ሪፖርተር ከአስተዳደሩ ያገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡