በደቡብ ኦሞ ዞን በመንግስት ልማት ፕሮጄክቶች የተሸፈነው የህወኃት ባለሥልጣናትና ጀሌዎቻቸው የሚፈጽሙት የመሬት ቅርምትና አንድምታው በዞኑ ባለሙያዎች ተጋለጠ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በደቡብ ኦሞ ዞን በመንግስት ልማት ፕሮጄክቶች የተሸፈነው የህወኃት ባለሥልጣናትና ጀሌዎቻቸው የሚፈጽሙት የመሬት ቅርምትና አንድምታው በዞኑ ባለሙያዎች ተጋለጠ:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
•የአገርና ህዝብ ሃብት በማስያዝ በዝቅተኛ ግምት ለመሬት ዝግጅት ብቻ ከ 635 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ተወስዷል፤
• የዞኑ ልማት፣የምግብ ምርትና የአካባቢው ነዋሪ ህይወት ተበድሏል፤
• የአካባቢው ባለሃብቶች ወደ ምርት ኢንቬስትመንት የመግባት ተነሳሽነት ወድቋል፤
• ሌሎች አልሚዎች ወደ ዞኑ ለመግባት የሚችሉበት ዕድል ተዘግቷል፤
በደቡብ ኦሞ ዞን መንግስት በስኳር ልማት ፕሮጄክቶችና በሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሥራ ያለየአካባቢ ተጽዕኖ ትንተና/ Environmental Impact Analysis / እና ማኅበረ -ኢኮኖሚ ስሱነት/ Socio.Economic Sensitivity / ዝርዝር ጥናት እንዲሁም ያለአካባቢው ነዋሪ ዕውቀት፣ተሳትፎና ይሁንታ የተጀመሩ ፕሮጄክቶች በህዝቡ ህይወት ላይ አደጋ ጋርጠዋል፡፡ ይህ የህዝቡን አመራረትና አኗኗር ከማወኩም በላይ ህዝቡን አፈናቅሏል፣ የህዝብ ቀጣይ ህይወት ዋስትና ለአደጋ ተጋልጧል፡፡ ህዝቡም ቅሬታውንና ተቃውሞውን በተለያየ መንገድ እየገለጸ መሆኑ፣ በዓለም አቀፍ የሰብዐዊ መብት ተሟጋቾችና የፍትሃዊ ዓለም ለሰው ልጆች ተቆርቋሪዎች እንዲሁም የአገር ውስጥ የፖለቲካ ድርጅቶቻና የሲቪክ ማህበራት ከረጅም ጊዜ አንስቶ በተደጋጋሚና በተለያዩ መድረኮችና መገናኛ ብዙሃን እየተገለጸ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በቅርቡ በኩራዝ አንድ የስኳር ልማት ፕሮጄክት ልማት አካባቢ የመንግስት ታጣቂ ኃይሎች በሱርማ ህዝብ ላይ የፈጸሙት ዘመኑን የማይመጥንና ለማመን የሚያስቸግር ኢሰብዐዊ ድርጊት ከኢትዮጵያዊያን አልፎ የኣለምን ማኅበረሰብ አሳዝኗል፣ እያነጋገረ ነው፣ የተቃውሞ ድምጾች ከየአቅጣጫው እየተደመጡ ነው፡፡ አምባገነኑ የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት ለእነዚህ የህዝብ እሮሮዎች ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት፣ ከህዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችንና የሚደመጡ ቅሬታዎችንና ተቃውሞዎችን በኃይል በማፈን አካሄዱ ጉዞውን መቀጠሉን ብቻ ሳይሆን በኢንቬስትመንት ስም/ከለላ ለአንድ ክልል የትግራይ ተወላጆች የማይታመን ይሉኝታ ቢስ አድልኦ እያደረገ መሆኑን በደቡብ ኦሞ ዞን እየሆነ ያለው በግልጽ ያሳያል፡፡
የዞኑ ባለሙያዎች ይህንን በዞኑ / በአካባቢው የማይታወቁና ቋሚ አድራሻቸውን የማይገልጹ፣ እንዲሁም የድጋፍ ደብዳቤ ከሚፈልጉበት ጊዜ ውጪ በአካባቢው የማይታዩ የትግራይ ተወላጅ ‹ የሃሰት ኢንቬስተሮች› የተከለለላቸውን ቦታና የኢንቬስትመንት ፈቃድ በማሳየት ብድር እንዲሰጣቸው የትብብር/ድጋፍ ደብዳቤ የተጻፈላቸው ፣ ጥቂት ቦታ ላይ ምንጣሮ ጀምረው አልምተናል በማለት የዞኑን ግብርናና ኢንቬስትመንት ቢሮ በሙስናና በማስፈራራት በማስመስከር ተጨማሪ ብድር እንዲሰጣቸው የተደረጉትን በማየት ማረጋገጥ ይቻላል ፡፡ ይህን ሁኔታ የተመለከቱ የዞኑ ኢንቬስትመንት ቢሮ ባለሙያዎች የእነዚህ ‹የሃሰት ኢንቬስተሮች› ዓላማ ልማት ሳይሆን ሁለት ዘዴዎችን በመጠቀም የጨበጣ የአገር ሃብት ዝርፊያ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ 1ኛ/ የህዝብና የአገር ሀብት በማስያዝ/ማሳየት በኢንቬስትመንት ስም ከባንክ ከፍተኛ ገንዘብ መውሰድ፣ 2ኛ/ ነገ የመሰረተ ልማት ወደ ዞኑ ሲስፋፋና ዞኑ ከማዕከል ጋር ያለው ግንኙነት ቢጠናከር ቦታውን ያለተፎካካሪ አስቀድመው መያዝ ፤ ሲሆን ሁለቱም በህግም በአሰራርም አግባብ ካለመሆናቸውም የአገርና ህዝብ ሃብት ዘረፋና ቅርምት፣ ከዚህም በላይ የአካባቢው ነዋሪዎችን የማፈናቀልና ከምርት በማስወጣት የዞኑን ልማት እንቅስቃሴና የምግብ ምርት/ ሰብልም ሆነ እንስሳት/ የሚጎዳ ነው ሲሉ ይተቻሉ፡፡ በዚህ መሰረት አንድ ሄክታር መሬት ለምርት ለማዘጋጀት በትንሹ እስከ 80 ሺህ ብር ፕሮፖዛል በማዘጋጀትና ከዚህ ውስጥ 30 ከመቶውን ብቻ በባንክ ስቴትመንት ላይ በማሳየት (ከተጠየቁ) በሄክታር እስከ 56 000 /ሃምሳ ስድስት ሺህ/ ብር ከመንግስት ባንኮች ( በተለይ ከልማት ባንክና ኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ) እንደሚበደሩ፣ በዚህ ስሌት መሰረት በ100 ሄክታር ብቻ 5 600 000/ አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ / ባለ ሺህ ሄክታሮችም እስከ  /ሃምሳ ስድስት ሚሊዮን ብር/ ብድር እንደሚጠይቁ ታውቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ይህንኑ የኢንቬስትመንት ስምምነትና የቦታ ፈቃድ፣እና የድጋፍ ደብዳቤ( ከክልልና ማዕከል በሚሰጥ ትዕዛዝ ጭምር በሚጻፍ) በማሳየት የተለያዩ የእርሻ መሳሪያዎች፣ ተሸከርካሪዎችና ኬሚካሎች ያለቀረጥ ከውጪ አስገብተው እንደሚሸጡ፣ ከአገር ውስጥ የሚመረቱትን በብድር እንዲሚቀበሉና ለሌላ አገልግሎት ወይም ሺያጭ እንደሚያውሉና ትርፍ እንደሚያጋብሱ ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ በዚህ የሌሎችን ባለሃብቶች የፉክክር አቅም በማዳከም ከልማትና ንግድ እንቅስቃሴኣቸው እንደሚያስወጧቸውና የአገሪቱን ኢኮኖሚ በበላይነትና በብቸኝነት የመያዝ ዕቅዳቸውን የማሳካት አካል እንደሆነ ፣ በዚህም ወደዞኑ ከእነርሱ ውጪ የሌላ ብሄረሰብ ባለሃብቶች እንዳይመጡ በማድረግ የዞኑን ልማት እንደጎዱት ባለሙያዎች ይገልጻሉ፣ በልማቱ ቢሰማሩ እንኳ አንዱን ልጅ ሌላውን የእንጀራ ልጅ በሚያይ ስርዓት በየቱም መስክ የሚደረግ ፉክክር ሚዛናዊና ፍትሃዊ ሊሆን አይችልምና ሌሎች ለመምጣት የሚያነሳሳቸውና የሚያደፋፍራቸው ሁኔታ ዝግ ነው፡፡
ይህን እውነት በሚለከተው ዳታ እንመለከታለን፡፡ በ2006 በዞኑ ያሉ ኢንቬስተሮች ብዛት 20 ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 16ቱ (80 ከመቶ) ፣እንዲሁም ከጠቅላላው ለግብርናና አግሮ ኢንዱስትሪ ከተሰጠውና በመጠን ከሚታወቀው(አንዱ ኢንቬስተር መሬት መጠን በዞኑ ኢንቬስትመንት ቢሮ አይታወቅም) 106 997.7 ሄክታር መሬት 105 914.6 ሄክታር (98.9 %) የተወሰደው/የተያዘው በእነዚሁ የሕወኃት አባላትና ደጋፊ የጥቅም ተጋሪ የትግራይ ተወላጆች ነው፡፡ ከዞኑ ነዋሪዎች በኢንቬስትመንት የተሰማሩት አራት (20 ከመቶ) ብቻ ሲሆኑ የያዙት መሬትም 1083. 1 ሄክታር (1. 02 %) ብቻ ነው፡፡ እነዚህ የትግራይ ተወላጆች ከያዙት መሬት 95 487 ሄክታር (89.2 %) በስኳር ፕሮጀክት ቦታ (ለአገርና ህዝብ የጋራ ጥቅም የተባለው እንኳ ጥያቄ እያስነሳ ባለበት) መሆኑ በቀጣይ ወደልማቱ ሲገባ/ቢገባ የሚፈነዳ የጊዜ ቦንብ እንደተቀበረ ያሳያል ይላሉ ባለሙያዎቹ፡፡ ከዚህ በላይ አስገራሚው እነዚህ የሃሰት ኢንቬስተሮች በስማቸው ለዓመታት ከያዙት መሬት ‹ያለሙት ›/ከተባለ/ ከአንድ በመቶ በታች 800 ሄክታር (0.75 %) ብቻ መሆኑ ከላይ የገለጽነውን የዝርፊያና የተንኮል አካሄድ ያረጋግጣል፡፡ የዞኑን የኢንቬስትመንት/ልማት እምቅ ኃይል የሚያሳየውን መረጃ ከየት እንዳገኙት የሚገረሙትና ከማዕከል 760 ኪ.ሜ.፣ ከክልላቸው ከ 1 500 ኪ፣ሜ በላይ ከሚርቀው የድንበር ዞን እንዴት እንደመጡ የሚጠይቁት ባለሙያዎች ይህ የህወኃት እጅ ከሌለበት የሚታሰብ አይደለም (አንድም የሌላ ብሄረሰብ አባል ያለመኖሩን ከግምት በማስገባት) ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠው ፣ግን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ እነዚህ የሃሰት ኢንቬስተሮች ከህወኃት የተለየ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው፣ በክልሉ ኢንቬስትመንት ቢሮ የሚደገፉ የሥርዓቱ ተጠቃሚዎች ስለመሆናቸው ግን በእርግጠኝነት ለመናገር ምርምር አያስፈልገውም፣ ግልጽ ነው ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ይህን ፕሮፖዛል መሰረት አድርገው ስሌት የሰሩ የዞኑ ባለሙያዎች የህዝብና አገር ሃብት በማስያዝ እነዚህ ‹የሃሰት ኢንቬስተሮች › በዞኑ በተቀራመቱት ቦታ ለመሬት ዝግጅት በሚል ብቻ እስከ / ስድስት መቶ ሰላሳ አምስት ሚሊዮን አራት መቶ ሰማንያ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ/ ድረስ ብድር ሊቀበሉ እንደሚችሉና ይህንንም ገንዘብ በሌላ የሥራ መስክ በማዋል ሌላውን በትክክለኛ መንገድ የሚሰራ ዜጋ ከፉክክር እንሚያስወጡት ገልጸዋል፡፡ ከዚህ 635 487 600 ገንዘብ እስካሁን በተሰራው ሥራ በዞኑ ‹በስራ ላይ ዋለ ከተባለ› የወጣው ገንዘብ ከ 5 ሚሊዮን 84 ሺህ ብር በታች እንደሆነና ቀሪው ከ 630 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ዞኑ እንዳልመጣ፣ ይህም ከቀረጥ ነጻ ከሚገቡና በብድር ከሚወሰዱ የእርሻ መሳሪያዎች፣ ተሽከሪካርዎችና ኬሚካሎች እንደማያካትት በቁጭት ይገልጻሉ፡፡
የዚህ ጽሁፍ መነሻ ማስረጃ ከሁለት ዓመት በፊት ነበረውን የሚያሳይ እንደመሆኑ አንዳንዶቹ የተሰራቺውን ጥቂት ሥራ በማቅረብና በማሳየት ለቀጣይ ስራዎች፣ ለማስፋፊያና የስራ ማስኬጃ በሚል ሌላ ተጨማሪ ብድር ለመጠየቅ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን እነዚሁ ምንጮች በአግራሞት ይገልጻሉ፡፡ ደቡብ ኦሞ ዞን ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች(ትግራይን ጨምሮ) የመጡ ነዋሪዎችም ሆኑ ለተለያየ ሥራ የሚመጡ ዜጎች በፍቅርና በመከባበር፣በጠንካራ ጤናማ ማኅበራዊ ቁርኝትና ትስስር ፣በመተሳሰብ …የሚኖሩበት ነው የሚሉት ባለሙያዎች እነዚህ በዞኑ የማይታወቁ እንደመስቀል ወፍ ብቅ ብለው የሚጠፉ ወይም በጉዳይ አስፈጻሚ በኩል ዞኑን የሚያውቁ ግን በዞኑ ህዝብ ሃብት ማስያዣነት የሚመዘብሩ የአንድ ብሄረሰብ ተወላጆች በዚህ መጠንና መንገድ ዞኑን መውረራቸው የስርዓቱን ለአንድ ብሄረሰብ መቆምና የሚደረገውን የዘር አድልዎ/በዘር ላይ የተመሰረተ ጥቅመኝነት/ ያመለክታል ብለዋል ፡፡ ይህ ዓይነቱ ዘረኛ አድልኣዊ የተንኮል አካሄድ በቀጣይ በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በተለይም ነገ ወደ ዞኑ ለትክክለኛ ኢንቬስትመንት በሚመጡ የትግራይ ተወላጆች ላይ የአካባቢው ነዋሪ የሚኖረውን አመለካከት የሚያዛባ ሊሆን እንደሚቺል ባለሙያዎቹ ሥጋታቸውን ገልጸዋል ፡፡ለዚህ ጽሁፍ ግብኣት የሆኑ መሰረታዊ መረጃዎችንና የባለሙያ ትንታኔ የሰጡንን የዞኑን የግብርና፣ የህብረት ሥራና የኢንቬስትመንት ቢሮ ባለሙያዎች እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ ምሁራን እናመሰግናለን፡፡ የጽሁፉ ደጋፊ የሆነው የዞኑን ኢንቬስተሮች ዝርዝርና የያዙትንና ያለሙትን መሬት መጠን የሚያሳይ ሰንጠረዥ ተያይዟል፡፡
በደቡብ ኦሞ ዞን በግብርናና አግሮ ኢንዱስትሪ ሥም የተወሰደና በ ‹ ሥራ ላይ የዋለው› መሬት መጠን ( 2006 ዓ.ም.)
1 ኦሞ ሸለቆ አግሮ ኢንዱስትሪ ጥጥ ልማት 5490 — በና ጸማይ
2 ሲሳይ ተስፋዬ አግሮ ኢንዱስትሪ ጥጥና የቅባት እህሎች 430 — ኛንጋቶም ጥጥና የቅባት እህሎች 430(b) — ኛንጋቶም
3 ናሩስ ባዮ ቴክኖሎጂ ፓልምና የቅባት እህሎች 10 027(b) — ኛንጋቶም
4 ሉሲ እርሻ ልማት ጥጥ ልማት 4 003(b) — ዳሰነች
5 ኤ.ኤ.ቲ.ጠ/ን/ኃ/የተ/የግ/ማ. ጥጥና የቅባት እህሎች 2 000(b) — ሳላማጎ
6 ጂ.ዋይ.ቢ፣ኤስ.ኃ/የተ/የግ/ማ. ጥጥና የቅባት እህሎች 1 500(b) — ሳላማጎ
7 ሳግላ ሓ/የተ/የገ/ማ. ጥጥና የቅባት እህሎች 1 500 100 0.067 በና ጸማይ
8 ኤን.ቲ.ኤስ.ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማ. አትክልትና ፍራፍሬ 300 100 ማሌ
9 ዳንኤል ፋሲል ጥጥ ልማት 50 027(b) 200 0. 3 ዳሰነች
10 አቶ አማኑኤል ገ/መድህን ጥጥና የቅባትእህሎች 1 000 — ደቡብ አሪ
11 አቶ ረታ ሃ/ማሪያም የቅባት እሎች 2 137.6 100 4 ሐመር
12 መላ እርሻ ልማት ጥጥና የቅባት እህሎች 5 000(b) — ዳሰነች
13 ጸጋዬ ደሞዝ ጥጥና የቅባት እህሎች 1 000(b) 300 30 ዳሰነች
14 ዶ/ር ጣዕመ ሐጎስ ጥጥና የቅባት እህሎች 5 000(b) —– ኛንጋቶም
15 አዳማ ዲቮለፕመንት ሃ/የተ/የግ/ማ. ጥጥ ልማት ያልታወቀ(b) —– ኛንጋቶም በክልል የተፈቀደ
16 ሳትኮን ሃ/የተ/የግ/እርሻ ጥጥ ልማት 16 500(b) — ሳላማጎ የዞን መንገድ ሥራ ተቋራጭ
17 ገበየሁ ምናሉ ጥጥና የቅባት እህሎች 300 100 0.33 በና ጸማይ
18 ጂንካ ደንና ቅመማቅመም ደንና ቅመማቅመም 150 – ደቡብ አሪ
19 ተፈሪና ልጆቹ እርሻ ልማት ቡናና ፍራፍሬ ልማት 133.1 87 ደቡብ አሪ
20 ሱዳሜል እርሻ ቡና ልማት 500 143 ደቡብ አሪ
ድምር 1 ( 1 – 16)@ 105 914.6 (98.9 %) 800 0.75%
ድምር 2 (17—20) 1083. 1 (1. 02 %) 330 30.4
ድምር ጠቅላላ (1—20) 106 997.7 ድምር (የስኳር ፕሮጁክት ወረዳዎች ጋር ቀጥታ የሚዋሰኑ) (b) 95 487 (89.2 %) ————————– @ —
ከተራ ቁጥር 1 እስከ 16 የተመለከቱት የትግራይ ተወላጆች ናቸው፡፡ በተራ ቁጥር 15 የተገለጸው ‹ ኢንቬስተር ›የያዘው ቦታ መጠን በዞኑ አይታወቅም፡፡ ከተራ ቁጥር 17 እስከ 20 ያሉት የአካባቢው ተወላጆች ሲሆኑ ከባንክ ያገኙት ብድር የለም፡፡ (b)— ከስኳር ልማት ፕሮጄክት ጋር በቀጥታ የተገናኙ ወረዳዎች/ ቦታዎች፣ በተጨማሪ የሀመር ወረዳም ከፕሮጄክቱ ጋር ይዋሰናል፡፡ አንድ ሄክታር 10 000 (አስር ሺህ) ካሬ ሜትር ነው ፡፡