በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታሥረዋል ተባለ ::(VOA)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አራት ወራትን ያስቆጠረው የኦሮሚያ ተቃውሞ አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች እንደቀጠለ መኾኑን ዘገባዎች እየጠቆሙ ነው። ከትናንት ወድያ ማምሻውን በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በነበረ ተቃዎሞ ተማሪዎች መታሠራቸው ተነሯል። የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት የታሠረ ተማሪ የለም ብለዋል።

አራት ወራትን ያስቆጠረው የኦሮሚያ ተቃውሞ አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች እንደቀጠለ መኾኑን ዘገባዎች እየጠቆሙ ነው። ትናንት ማምሻውን በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ተቃውሞ እንደነበርና ተማሪዎች መታሠራቸውን የዐይን እማኝ መኾኑን የገለፀ ተማሪ ተናግሯል።

ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ

ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ

የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት በበኩላቸው ተቃውሞ ያሰሙት ተማሪዎች ቁጥር ከሰላሳ እንደማይበልጥ ይናገራሉ፡፡ በተያያዘም በጉጂ ዞን ሊበን ወረዳ ከተለያዩ ቀበሌዎች ሰዎች እየታሠሩ መኾኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ የክልሉ ፖሊስ ምንም የታሠረ ሰው የለም ይላል።

የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ባልደረባ ጃለኔ ገመዳ እና ሶራ ሀለኬ ያጠናቀሩትን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋለች።

http://av.voanews.com/clips/VAM/2016/03/15/c44c57ef-958b-4529-bfa3-b6a1309e8838.mp3?download=1