ተንጋለው ቢተፉ : ተመልሶ ባፉ – ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው::ቀብሮ ብቻ ሳይሆን አቃጥሎ አመድ አድርጎ ነው::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ተንጋለው ቢተፉ : ተመልሶ ባፉ – ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው::ቀብሮ ብቻ ሳይሆን አቃጥሎ አመድ አድርጎ ነው::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎OromoProtests‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎EthiopianOppositionparties‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi – Ethiopian DJ – ከሶማሊያ ከኬንያ እና ከደቡብ ሱዳን እያስኮበለሉ ልዩ ሃይል እና የፌዴራል ፖሊስ አድርጎ በመቅጠር ኢትዮጵያዊ ዜግነት መስጠት ምን የሚሉት በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ላይ እየተደረገ ያለ ጥላቻ ነው ??? ከደህንነት ቢሮ የሚወጡ ጥቆማዎች አስደንጋጭ ናቸው::ወያኔ ጊዜ መግዣ ፋታ ማግኛ ማዘናጊያ ማደናበሪያ ያላቸውን የፕሮፓጋንዳ ስራዎች እየሰራ ነው:;የወያኔን አካሄድ ጠንቅቀን ማወቅ አለብን ዝም ብሎ ፖለቲከኛ ነኝ አያሉ ማራገብ አክቲቭስት ነኝ እያሉ መብጠልጠል/ማጦልጦል ጥቅም የለውም::ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው::ቀብሮ ብቻ ሳይሆን አቃጥሎ አመድ አድርጎ ነው::ካልሆነ ጊዜ ገዝቶ እያዘናጋ የለውጥ ሃይሉን አመድ ለማድረግ ቆርጧል::

ሁሉም ነገር ስህተት ነው ብለው ራሳቸው አምነዋል ከተባለ እነዚህ ሰዎች ስልጣን የማለቁበት ምክንያት ምንድነው? የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን.. የኦሮሞ ወገኖኔ ላይ የወሰዱት ድድብና የተሞላበት ግድያና ድብደባና እስር … የትራፊክ ሕግ … የጤና መድህን ዋስትና … ሁሉ ፖሊሲያቸው ስህተት ነው እያሉ እየተናገሩ ነው::በአገራችን ላይ አስተዳዳሪ ነን ብለው እስከተቀመጡ ድረስ ሃገርና እና ሕዝብን የሚመሩበት ፖሊሲ ስህተት እና ፉርሽ ከሆነ ምን እየጠበቅን ነው::ሕዝብ ላይ እየደነፉ ሕዝብ ላይ እያሾፉ ሕዝብን እየዋሹ ከዚህም አልፈው እየገደሉ እያሰሩ እያሳደዱ ይህ ስራችን ስህተት ነው እያሉ ደጋግመው እያደረጉት እኛ ግን ምን እየሰራን ነው?እነሱ ሰው ለመጨፍጨፍ በአንድነት ሲዘምቱ ደግመው ለለመዋሸው በአንድነት ሲደሰኩሩ እኛ ስለ ነጻነታችን ምን እየሰራን ነው?ድር ቢያብር አንበሳ ያስር አንድ እንጨት ብቻውን አይነድም::

ኢሕአዴግ ተሃድሶ አያስፈልገውም በስብሷል መፍረስ አለበት::እኛ አይደለንም ራሳቸው አመራሮቹ ድርጅታቸው እንደበሰበሰ ከሟቹ ጀምሮ ተናግረውታል::አሁን ያለው አመራር ሰው ያልተረዳለት ነገር ቢኖር ራሱን የሚክበው በባዶ ነው:: ሕዝብን እያስገደለ የሚገኘው ያልተማሩ በፕሮፓጋንዳ የተሞሉ ያልሰለጠኑ ፖሊሶችን ከአንዱ ክልል ወደ አንዱ ክልል እየወሰድ ነው::ለመሆኑ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን ? 25 ሺህ የልዩ ሃይል ፖሊስ ሰራዊት ከሶማሊያ ከደቡብ ሱዳን እና ኦሮሚኛ ተናጋሪ ከሆኑ ኬንያውያን ተመልምለው ሰልጥነው ከፌዴራል እና ከክልል እንዲሁም ከአግኣዚ ሰራዊት ጋር ተደባልቀው ሕዝብ እየገደሉ ይገኛሉ አሁንም ስልጣንን ከሕወሓት ሚሊሻዎች ጋር በጋራ ይጠብቃሉ የተባሉ ከየቦታው እየተመለመሉ እየሰለጠኑ ይገኛሉ::ግን እስከመቼ??? ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.